User:IRAN AT A GLANCE/sandbox

From Wikipedia, the free encyclopedia

ኢራን[edit]

ኢራን 1,648,195 ኪ.ሜ2 ስፋትና 70,495,782 የህዝብ ብዛት ያላት ሀገር ናት።  በሰሜኑ ወይና ደጋ የአየር ንብረት ውስጥ በስተደቡብ ስፍራ ላይ፣በመካከለኛው ምስራቅ ውስጥ፣ከ250 00’ እስከ 390 47 ሰሜናዊ ላቲቲዩድ እና ከ440 02’ እስከ 630 20’ ግሪንዊች መካከል ትገኛለች።[1]

ሰሜን ቴህራን
ሰሜን ቴህራን

ኢራን ከቱርክሚንስታን፣ አዘርባጃንና አርሜንያ ጋር በስተሰሜን በኩል፤ ከአፍጋኒስታንና ፓኪስታን ጋር ደግሞ በስተምስራቅ እንዲሁም ከኢራቅና

ቱርክ ጋር ደግሞ በምዕራብ በኩል ትዋሰናለች። የአለማችን ትልቁ ሀይቅ

የሆነው የካስፒያን ባህር ከኢራን በስተሰሜን ሲገኝ፤የፐርሽያ ሰላጤ (ከኦማን ባህር ትይዩ) ደግሞ ከኢራን በስተደቡብ ይገኛል። የሀገሪቱ  የውስጥ ጉዳይ ሚንስትር በቅርቡ በ2010 ባወጣው መረጃ መሰረት ኢራን 31 ግዛቶችና 387 ከተማ ቀመስ ሥፍራዎች አሏት። እያንዳንዱ ግዛት የተለያዩ ከተማ ቀመስና ወረዳዎች አሉት።  በወረዳ ውስጥ  ከተሞችና መንደሮች ትንሾቹ ቦታዎች ናቸው።

ኢራን በተለያዩ መልክአ ምድራዊ ምክንያቶች አራት አይነት ወቅቶች ያላት ሀገር ናት። ለእነዚህ የተለያዩ መልክአ ምድራዊ ገፅታዎቿ ከአውሮፓ፣ ከሜድትራንያን ባህር፣ ከአፍሪካ የሰሀራ በርሃ፣ ከህንድ ውቅያኖስ፣ ከኢስያ ውስጣዊ ከፍተኛ ስፍራዎች እና ከቀዝቃዛ የአየር ፀባይ አካባቢ አጠገብ መገኘቷ አንዱ ምክንያት ነው። በተጨማሪም ሰፊ ቦታ፣ የበዙ ተራሮችና የበረሃ ስፍራዎች እንዲሁም በሀገሪቱ በስተደቡብና በስተሰሜን በኩል ሁለት ትላልቅ ባህሮች መኖራቸው ኢራን የተለያዩ አይነት የአየር ፀባያት እንዲኖራት አስችሏታል።  እነዚህ የተለያዩ የአየር ፀባያት በሦስት ሊከፈሉ ይችላሉ። እነዚህም ደረቅና ከፊል ደረቅ፣ ቀዝቃዛ ተራራና የወይን አደጋ ተራራ እና ካስፒያን ናቸው።

“ኢራን” የሚለው ቃል አርያኖች ወደ ከፍተኛው ስፍራ ከመጡበት ጊዜ ጀምሮ ከቦታው ታሪክ እኩል የቆየ ስያሜ ነው። በመካከለኛው የፐርሽያ ቋንቋ ስያሜው ‹ኤራን› የሚል የነበረ ሲሆን ይህም ‹አርያናም› ከሚለው ከጥንቱ የኢራኖች ቋንቋ የተገኘ ነው። እንደ ተወሰኑ አጥኚዎች እምነት “አርያን” የሚለው ስያሜ (በጥንቱ እንዲካ አርያ፣ በጥንቱ ኢራንያን አርያ፣ በጥንቱ ፐርሽያ አርያ እና በአቬስተን ኢሪአ) ትርጉም “ምርጥ” ማለት ነው። የዚህን አካባቢ ታሪክ በግሪክና ላቲን ፅሑፎች ውስጥ በምንፈልግበት ጊዜ የምናገኘው ኢራን ከሚለው ቃል ይልቅ ከግሪኩ “ፔርሲአ” ከሚለው ቃል የመጡትን “ፔርስ” ወይም “ፔርሱን” የሚሉትን ቃላት ነው። ከ1935 (እ.አ.አ) ጀምሮ ግን ሀገሪቱ በአለም አቀፍ መድረክ “ኢራን” ተብላ መጠራት ጀመረች።[2]


ጥንታዊው የኢራን ምድር በአሁኑ ሰአት 31 ግዛቶች ያሉት ሲሆን እያንዳንዱም የራሱ የሆነ የተለያዩ ታሪካዊ፣ መልከዓምድራዊና ባህላዊ ገፅታዎች ያሉት ቢሆንም ህዝቡ ግን አንድና የተዋሀደ ነው። በብሄራዊው የ2006 የህዝብ ቆጠራ መሰረት በእነዚህ 31 ግዛቶች ውስጥ ከ83,992,949 የሚበልጥ ህዝብ አለ። አማካኝ እድሜ 77.33 ነው። ሴት 50.49 በመቶ፣ ወንድ 49.51 በመቶ ናቸው። የሀገሪቱ መገበያያ ገንዘብ “ሪያል” ነው። የሀገሪቱ ብሄራዊ ሀይማኖት እስልምና ሲሆን አብዛኞቹ ሰዎች ሙስሊሞች ናቸው። ከዚህ በተጨማሪ ግን የራሳቸው የሆነ በዓላትና ሀይማኖትዊ ክንውኖችን በነፃነት የሚያከብሩ አናሳ የሆኑ የክርስትና፣ የአይሁድና የዞሮስቴሪያን እምነት ተከታዮችም አሉ።

የዚህ ምድር ነዋሪዎች ከጥንት ጀምሮ በተለያዩ ጊዜያት በተለያዩ የታሪክ ክስተቶች ውስጥ አልፈዋል። በጊዜ ሂደት ብዙ ስርወ-  መንግስታት ወጥተው ወርደዋል። በሜድያን፣ በአካሜንድ፣ በፐርቲያንና በሳሳኒድ የአስተዳደር ጊዜያት ኢራን የአለም ልእለ-ሀያል ሀገር ሆና ነበር። በመጨረሻም ብዙ ባህልና ስልጣኔ ያላቸው ህዝብ  ሆነው ወደ እስልምና ሀይማኖት ገብተዋል። እነ ሳማኒድ፣ ክዋርዝሚድ፣ ሳፋቪድ፣ አፍሻሪድ፣ ዘንድ እና ቃጃር ስርወ-መንግስታት በነበሩበት ባለፈቱ 15 መቶ ክፍለ ዘመናት ውስጥ በፍልስፍናውና በሳይንሱ ረገድ ድንቅ የሆነ የእድገት ደረጃ ላይ ደርሰው ነበር። በእነዚህ ዘመናት ውስጥ ኢራናውያን ለሀገራቸው ደማቸውን አፍሰዋል፤ በሀገሪቱን እድገት፣ ሀይማኖታዊነት እና ክብር ላይ ያነጣጠረን አደጋ ሁሉ መክተዋል።

በኢራን የተደረገው የእስልምና አብዮት ህዝቡ ከከፈላቸው መስዋእቶች መካከል የቅርቡ ጊዜው ሆኖ ሊጠቀስ ይችላል። በ1960ዎቹ የተቀጣጠለው የእስልምና አብዮት ኢማም ኾሜኒ በፌብሩዋሪ 1 1979 ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ በድል ተጠናቋል። በአስር ቀናት ውስጥ ብቻ (ማለትም በፌብሩዋሪ 11 1979) አብዮቱ ተጠናቀቀ። በኤፕሪል 1 1979 በተደረገው ሪፈረንደም መሰረት 98.2 በመቶ የሚሆነው ህዝብ ደግፎትና መርጦት የኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ ተቋቋመ። ከዚህ ጊዜ ጀምሮ በዚች ጥንታዊ ምድር በኢማም ኩመይኒ መሪነትና በአያቶላህ ካሜኒ ተተኪነት አዲስ ዘመን ተበሰረ።

የገዢዎቹ ተቀዳሚ አላማዎች የሚባሉት ገለልተኛነት፣ ነፃነት፣ የወሰን መከበር እና የኢራንን እስላማዊነት መጠበቅ ናቸው። ለ8 አመታት በዘለቀው በኢራቅ የጦርነት ጊዜያት እንኳን የህዝቡ ቀናኤነት ለአፍታ እንኳ አልተፈታም ነበር። በአሁኑ ወቅትም ቢሆን ኢራን ጥሩ ደረጃዎችን በማለፍ ብሩህ ተስፋ ወዳለው ጊዜ በመገስገስ ላይ ትገኛለች።[3]

  1. ^ Sabzian, Mojgan (2010). Iran Tourism: The Comprehensive Book. Iran: Kamel Publications Co. p. 25. ISBN 978-964-439-596-3.
  2. ^ Sabzian, Mojgan (2010). Iran Tourism: The Comprehensive Book. Islamic Republic of Iran: Kamel Publications Co. pp. 31–32. ISBN 978-964-439-596-3.
  3. ^ Hamid, Ansari (2010). The Awakening Hadith- Amharic. Tehran - Iran: Alhoda international publishers. p. 100. ISBN 978-964-439-450-8.

አዘርባዬጃኔ ቃርቢ[edit]

አዘርባዬጃኔ ቃጋርቢ (ምዕራብ አዘርባዬጃን) ግዛት በሰሜን ምዕራብ የኢራን አካባቢ ሲገኝ፤ ከቱርክ፣ ኢራቅና አዘርባጃን (የናክቺቫን ራስገዝ) ጋር ተጎራባች ነው።  በክረምት ከፍተኛ የሆነ የበረዶ ግግር ይከሰታል። በዚህ አካባቢ አቭረን (በኮይ)፣ ባርዴራሽ (በአሩሚዬህ)፣ሳሪ ዳሽ (በአሽናቪዮህ) እና ማሌክ ሄላን (በፒራን ሻህር) የመሳሰሉ ትላልቅ ተራሮች ይገኛሉ። ይህ ግዛት ከፍተኛ የሆነ የውሃ እና የማዕድን ክምችት አለው።[1]

የምእራብ አዘርባይጃን ግዛት ስነተፈጥሮ ኢራን
የምእራብ አዘርባይጃን  ግዛት ስነተፈጥሮ ኢራን


ለም የሆነው የደን ስፍራው 174,000 ሄክታር ያህል ቦታን የሚሸፍን ሲሆን አፈርን በመጠበቅ፣ የዱር እንስሳትን በማስጠለል፣ የርጥበት መጠንን በመቆጣጠርና የአፈር መሸርሸርን በመከላከል ጠቀሜታም አለው።  በዚህ አካባቢ ያሉት ተክሎች የተለያየ አይነት ያላቸው በመሆኑ ለማር ምርት አመቺ ነው።

እስከ ታላቁ አሌክሳንደርና ተከታዩ ግኝት ጊዜ ድረስ አዛርባዮጃኔ ጋርቢ የጥንቷ የሜድስ ግዛት  አካል የነበረች ሲሆን “ትንሿ ሚዲያ” በመባልም ትታወቅ ነበር። ከእየሱስ ልደት በፊት በ331 ማለትም ታላቁ አሌክሳንደር ኢራንን በሚያስተዳድርበት ወቅት ይህቺን ግዛት ከግሪክ ቁጥጥር የነጠቀው የትንሹ ሜዲያ ግዛት አስተዳዳሪ የነበረው ኢራናዊ ኮማንደር አቶርፓት ወይም አቶርፓታን (በእሳት የታጠረ) ነበር። ከዚህ በኃላም ህዝቡ ለዚህ ሰው ጀግንነት ያለውን አድናቆት ለመግለፅ፤ ትንሿን ሜዲያ “ጀኔራል አቶርፓት” አሏት። በኃላ ላይ ደግሞ አዛርባደጋንና አዘርፓትካን ተባለች። በሳሳኒድ ሥረወ-መንግስት ጊዜ በኢራን ውስጥ ታዋቂ ከነበሩ ዋነኛ ግዛቶች አንዷ ነበረች። ታዋቂ የእሳት ማምለኪያ ስፍራዎች ይገኙባት ስለነበርም አዘርባዮጃን ትባል ነበር።

በዚህ አካባቢ አዜሪዎች፣ ኩርዲሾችና አርሜንያኖች መገኘታቸው ግዛቷን የህብረተሰብ ትይንት መድረክ አድርጓታል። ጎሳዎች በአዛርባዮጃኔ ጋርቢ የህዝቡ አንድ ሦስተኛ ናቸው።  በዬይላቅ ሥፍራ ከፍየል ቆዳ የሚሰራ ሲያህ ካዶር የተባለ ጥቁርና ቡናማ ድንኳን ይጥላሉ።

የአዘርባዮጃን ባህላዊ ሙዚቃ ህዝቡ በዕለት-ተዕለት ኑሮው ውስጥ የሚያጋጥሙትን ጉዳዮች ማለትም አንድነትን፣ መነጣጠልን፣ ድልን፣ ሽንፈትን፣ ጅግንነትን፣ ደስታንና ሀዘንን ያንፀባርቃል። ሌዝጊ በሚባለው የአዛሪዎች ተወዳጅ ዳንስ እንኳ የሀዘን ስሜትን ግልፅ ባልሆነ መልኩ በውስጡ ይዟል። ሥለ አዛርባዮጃኔ ሻርቂ ግዛት በሚቀርብበት ክፍል ውስጥ ስለዚህ ዘፈን ብዙ ባህሪያት ተጠቅሷል።[2]

በዚህ ግዛት ውስጥ የቱርክ ኬባብ፣ አሼዱግ (የእርጎ መረቅ) እና ኩፍቴህ ካሩን የሚባሉ ምግቦች ተዘውታሪ የምግብ አይነቶች ናቸው። የተቀሩት ምግቦችና ኩኪሶች አዛርባዮጃኔ ሻርቂ አካባቢ ከሚገኙት ጋር ተመሳሳይ ናቸው። ከዚህ አካባቢ የሚገኙት የግብርና እና የእንሰሳት ተዋጾዎች በመላው ኢራን እጅግ ታዋቂና ተወዳጆች ናቸው።

ከአዛርባዮጃኔ ጋርቢ ታዋቂ የእደ-ጥበብ ውጤቶች መካከል የቆዳ (ላይ) ሥራዎች፣ ሴርማህ ዱዚ የሚባለው የሰፊት አይነት፣ ቫርኒባፊ እና ጊቬህባፊ  የሚባሉት የሸመና አይነቶች፤ ጃጂም እና ከሱፍ ጨርቅ የሚሰራ ሆኖ ከቁርጭም ጭሚት እስከ ጉልበት ድረስ ሚሸፍነው ባሬኸባፊ ተጠቃሾች ናቸው።

  1. ^ Sabzian, Mojgan (2010). The Comprehensive Book. Islamic republic of Iran: Kamel Publications Co. p. 5. ISBN 978-964-439-596-3.
  2. ^ Sabzian, Mojgan (2010). The Comprehensive Book. Islamic republic of Iran: Kamel Publications Co. pp. 5–6. ISBN 978-964-439-596-3.

አዛርባዮጃኔ ሻርቂ[edit]

ምስራቃዊ አዘርባጃን ጠቅላይ ግዛት
ምስራቃዊ አዘርባጃን

የአዛርባዮጃኔ ሻርቄ (ምስራቅ አዛርባጃን) ግዛት በኢራን የስሜን ምዕራብ አካባቢ የምትገኝ ሲሆን ከኣዛርባጃን፣ አርሜንያና ከናክሺቫን ራስጋዝ ጋር ትዋሰናለች። በስተሰሜን የሚገኘው የሜድትራንያን ቅዝቃዜ እና ከካስፒያን አየር ፀባይ ጋር ተጨምሮ የዚህ አካባቢ ተራሮች ቀዝቃዛ ሲሆኑ ዝቅተኛ ቦታዎቹ ደግሞ የወይን አደጋ ፀባይ ኣላቸው። 17 ጉብታዎች ያሉትና ከ 3000 ሜ በላይ ያሉት የሰሃንድ ከፍተኛ ስፍራ የዚች ግዛት ከፍተኛው ቦታና በቋሚነትም የውሃ ሀብት መገኛ ነው። [1]

የቮልካኖ ፋንዳታ ውጤት የሆኑትና 4,811 ሜ ከፍታ ያላቸው የሶላታን ሳቫላን ጉብታዎችን የያዘው ሳበላን በአለማችን ውስጥ ከሚገኙ አስገራሚ ተራሮች ተርታ ተመድቧል። ብዙ ምንጮችን የያዘው የቦዝጉሽ የተራራ ስንሰለት ለአይደግሙሽና ቃራን ወንዞች መንፈላሰሻ አልጋ ነው። ከኢራን የደን ሀብት 1.2 በመቶ የሚሆነው የሚገኘው በዚህ አካባቢ ነው። በዚህ አካባቢ ያሉ ዋነኛ የደን ሀብት መገኛ ስፍራዎች የሚገኙት በአሃርና በካሌይባር ከተሞች ነው። ፍሰታቸው በኢራን ወስጥ ብቻ ከሚወሰኑ ሀይቆች ትልቁ የሆነው የኦሩሚየህ ሀይቅ በአዘርባዮጃኔ ሸርቄና በአዛረባዮጃኔ ጋብሪ ግዛቶች መካከልና ከፐርሺያ ከፍተኛ ቦታ በስተሰሜን ምዕራብ አቅጣጫ ይገኛል።ይህ ግዛት የጥንቱ የሜዴስ ምድር አካል የነበረ ሲሆን ታሪካዊ ሂደቱም በስተምዕራብ በኩል ከሚጎራበተው የአዘርባዮጃኔ ጋርቢ ግዛት ጋር ተመሳሳይነት አለው። በ1040 እ.አ.አ. የሴልጁክ ቱርኮች ወደ አካባቢው መምጣትን ተከትሎ የዚህ ግዛት ሰዎች ዘዬ በሂደት ከቱርክኛ ጋር መመሳሰል ችሏል።[2]

የአዛርባዮጃኔ ደርቂ ነዋሪዎች በማርች 21 የሚጀምረውን የአራንያውያንን አዲስ አመት (ኖውሩዝ) ለማክበር የተለያዩ ዝግጅቶችን ያደርጋሉ። ጥንታዊ የአሬናውያን የእሳት ክበረ-በዓል የሆነውን ቻሀርሻንቤህ ሱሪን ሁልጊዜ በአመቱ የመጨረሻ ረቡዕ ማታ ይከበራል። የሚወርደውን ውሃ እየዘለሉት ‹ገደቢሱ ረቡዕ ይጥፋ!› ይላሉ። አንዷ ሴት የሌላኛዋን ሴት ጣት ‹‹ካርሻንቤህ ካቱን›› በማለት በሊጥ ቀብታው ከስሩ መስታወትና ማበጠሪያ ታስቀምጣለች። ይህ ስርዓት እንግዲህ በክረምቱ መጨረሻ ቀናት ላይ የመሬት ለምት ባህሪን ለማመላከት ነው። በቁሪጃን መንደር አነስተኛ ሻማን በማስቀመጫው ላይ ለኩሳ በውሃ ላይ


እንዲንሳፈፍ ታደርገዋለች። በኖውሩዝ ጊዜ እየተዘዋወሩ የሚዘፍኑ ሙዚቀኞች በከተማና በመንደር ውስጥ በመዞር አጓጊው የፀደይ ወቅት መዳረሱን ያበስራሉ። በእስልምና ካላንደር የመጀመሪያው ወር በሆነው የሙሀረም ወር ሻክሴ የቫዝሴይ (አወይ ነጉስ ሁሴን / ወይ ሁሴን ማለት ነው) የሚባል የሀዘን ክብረ-በዓል አላቸው። በዚህ የሀዘን ክብረ-በዓል ላይ አንዳንድ ሰዎች ፊታቸውንና ጭንቅላታቸውን በጭቃ ወይም በከሰል የሚቀቡ ሲሆን ይህም የሚሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ለማመላከት ነው። ፈረሶቻቸውንም የኢማም ሁሴን ፈረስ አጊጣበት በነበረበት መልኩ ያስጌጧታል።

የሻህ ሳቫን እና አረስበራን ጎሳዎች እርስ በርሳቸው በጣም የሚደጋገፉና ልዩ የሆነ ታሪክ እንዲሁም አስደሳች ማህበራዊና ባህላዊ እሴቶችን የሚጋሩ በዚህ ግዛት ውስጥ የሚገኙ ዋነኛ ህዝቦች ናቸው። አየሩ በጣም ሲሞቅባቸውና በጣም ሲቀዘቅዝባቸው ለማረፊያነት የሚጠቀሙበት የራሳቸው የሆኑ ልዩ ስፍራዎች አሏቸው።

የምስራቅ አዘርባጃንጃ ካርታ
የምስራቅ አዘርባጃንጃ ካርታ

በዚህ የሀገሪቱ ግዛት አካባቢ ጀሮ-ገብ የሆኑ ዘፈኖች፣ የሚገርም የአዘፋፈን ስልት፣ የሚደንቅ ቅንብር፣ ጥልቅ ትርጉም ያላቸው ዘፈኖችና ተሰረቅራቂ የዘፋኞች ድምፅ የሞላበት ነው። የመስኩ አጥኚዎች በአዛርባዮጃን ያለውን ሙዚቃ በሚከተለው መልኩ በ5 ይከፍሉታል፡-


1. ባህላዊ ሙዚቀኞች የሚያዘጋጁት አሺቆላር

2. ብሄራዊ ዘፈን የሆነው ካልቅ ማሂንላሪና ሞቃምላር

3. የሀዘን ጊዜ እና የሀይማኖት ዘፈን የሆኑት ታዕዚያ ሙዚቂ

4. በዕለት ተዕለት ስራ ላይ የሚንጉረጎሩት አማክ ማሂንላሪ

5. የሰርግና ጭፈራ ዘፈን የሆኑት ቶይ ዱዮን ሙዚቂ

የዚህ አካባቢ ተጠቃሽ የዕደ-ጥበብ ውጤቶች የሆኑት፡ ምንጣፍ፣ የሚያምር ዲዛይን ያሉት የሽመና ጨርቅ (ማስናድ)፣ ቫርኒ፣ ኪሊም፣ ሸክላዎች፣ ሴራሚኮች፣ የብርጌጦች፣ ጌሬህቺኒ፣ ቅርጫት ስራዎች ወይም ሩዱዚ የሚባለው በሀገር ጥልፍ የተሸፈነ ልብስ።[3]

ቼሎ ካባብ የኢራን ብሔራዊ ምግብ
ቼሎ ካባብ የኢራን ብሔራዊ ምግብ

ከምግበች ደግሞ ታቢሪዚ ኼባብ፣ ኩፋቴህ ታብሪዚ (ትልቅ የተድቦለቦለ ስጋ)፣ ፒቻቅ ቄይሜህ (ኬባብ ሆኖ ከደቃቅ ስጋ የሚሰራ)፣ ሬሽቴህ ፓሎቄሲ (ሩዝ በደረቅ) ዶሮ ማጅ (ዳቦ፤ አይብና ቅቤ)፤ ቃርኒያሪክ (የተከተፈ ስጋ፣ በዛ ያለ ነጭ ሽንኩርት፣ ‹‹ኤግፕንትና›› ‹‹ፓርሰሌይ››)፣ ኪንጋል (የተከተፈ ስጋ፣ እርጎ፣ ‹‹ሻሎት›› ሊጥና ብዙ ነጭ ሽንኩርት)፣ ዱሻ ማህፓሎ (ሩዝ፣ ‹‹ሳፍሮን›› ና ዶሮ) እንዲሁም የተለያዩ የመረቅ አይነቶች፣ የፈላ ጭማቂ እና ዶልሜህ (በፍራፍሬ የተሰራ) ዋነኞቹ ናቸው።

  1. ^ Sabzian, Mojgan Sabzian (2010). Iran Tourism: The Comprehensive Book. Islamic republic of Iran: Kamel Publications Co. p. 6. ISBN 978-964-439-596-3.
  2. ^ Sabzian, Mojgan (2010). Iran Tourism: The Comprehensive Book. Islamic republic of Iran: Kamel Publications Co. p. 5. ISBN 978-964-439-596-3.
  3. ^ Sabzian, Mojgan (2010). Iran Tourism: The Comprehensive Book. Iran: Kamel Publications Co. p. 7. ISBN 978-964-439-596-3.

አርዳቢል[edit]

[1]አርዳቢል በኢራን የሰሜን ምዕራብ አካባቢ የሚገኝ ሲሆን ከአዘርባጃን ጋር በስተሰሜንና በስተምስራቅ በኩል ይጎራበታል። ሁለት ሦስተኛው የሚሆነው  የአርዳቢል ክፍል ተራራማ ሲሆን ቀሪው ክፍል ብቻ ነው ዝቅተኛ ቦታ። በተራራማውና በዝቅተኛው ስፍራዎች ያሉት 64 በመቶ የሚሆኑት ስፍራዎች ለከብቶች ምግብ የሚመች ሲሆን፣ 34 በመቶው ለእርሻና ለመኖሪያነት የሚያገለግል ነው። ቀሪው 2 በመቶ ደግሞ በደን የተሸፈነ ቦታ ነው። 4,811 ሜ ርዝመት ያለው የሳባላን (በአዛሪ ዘይ ሳቫላን) ግዙፍ ተራራ ከዳማሽን ቀጥሎ በአራን ውስጥ ሁለተኛው ረጅም ተራራ ነው። በግዛቱ በስተምስራቅ በኩል ከሰሜን እስከ ደቡብ የተዘረጋው የታሌሽ (ወይም ባግሩ) ከፍተኛ ቦታ የካስፒያን የባህር ዳርቻን ከአዘርባጃን ተራሮች ይለያል። ከካልካሊ በስተደቡብ የሚገኘው የአቀደቅ የተራራ ጫፉ በዚህ አካባቢ ከሚገኙት ሁሉ ግዙፉ ነው። በታሌሽ የተራራ ስንሰለቶች በኩል የሚያልፈው ዝነኛው የጋርዳሄይ ሄይራን መንገድ የአረዳቢልንና የጊላን ወረዳዎች ዋነኛ አገናኝ ነው። የቡዝጉሽ ተራራ በአርዳቢል የሚገኝ ሌላኛው ግዙፍ ተራራ ነው። በትልቁ የሞጋን ክፍል ውስጥ ጥቂቱን ክፍል የሚይዘውና 350.000 ሄክታር ስፋት ያለው የምጋን ለምለም ስፍራ የሚገኘው በአርዳቢል ሲሆን ለአዜሪ አርብቶ አደሮች ለከብቶቻቸው የክረምት ግጦሽ በመሆን ያገለግላል። ቃራህሱ፣ ከያቭቻይ፣ ባሌቅሉ ቻይ፣ ናሚን ቻይ፣ ኒርቻይ እና ቁሪቻይ ወደ እራስ ወንዝ የሚፈሱ ወንዞች ናቸው። በዚህ ግዛት ውስጥም ሸራቢልና ኒዎር የሚባሉ ሁለት ሀይቆች ይገኛሉ።

ከእስልምና መግባት በፊት የአረዳል ስም እርቬል ወይም አርታቬት ይባል ነበር። ኣርዳቢል የሚለው ስያሜ ከመካከለኛው እስከ መጨረሻው የሳሳኒድ ጊዜ ድረስ የአዘርባዮጃኔ ዋና መዲና ነበረች። በሳሳድና በመጀመሪያዎቹ የእስልምና ጊዜያት በፓህላቪ የተሰጠው አትራ የሚለው የቁልምጫ ስም አዘርባዮጃኔን የሚወክል ይመስላል።  ለብዙ ክፍለ ዘመናት ከፍተኛ ተራሮቹ፣ አረንጓዴው ተዳፋቶች (ዬይላቅ) እና ሰፊው የሞጋን ደለል (ቄሽላቅ) ለኢል ሳፋን እና በስሩ ላሉ 43 ንዑስ ጎሳዎች ምቹ የመኖሪያ ሁኔታ አመቻችተውላቸዋል።


በክረምት ውስጥ በሚደረገው የቼሌህ ኩቻክ ክብረ-በዓል ላይ በዚህ አካባቢ የሚኖሩ ሰዎች በጣራቸው ላይ እንጨት በማንደድና ወደ ስማይ በመተኮስ ሀይለኛ ጩኸትን ይፈጥራሉ። ይህን የሚያደርጉት በአዜሪ ዘይ ቃሪናና የምትባለውን ‹‹የቅዝቃዜ እናትን›› ለማስፈራራት ነው። በአመቱ የመጨረሻ ማክሰኞ ምሽት ላይ የአካባቢው ሰዎች በሆሌድ ድንጋይ (ዳሊኪ ዳሽ) አጠገብ በማለፍ ስለት ይገቡና ይህም ከተሳካ ኩኪስ ያድላሉ። በአሸበረቀ ልብስ ያጌጠች ተኩላ ተከም በመባል ትታወቃለች። የዚችን እንሰሳ ምስል የያዘ ሰው ከቦታ ቦታ በመሄድና የሚያምር ዘፈን እየዘፈነ የፀደይ መምጣትን ያበስራል። በሙሀረም (የእስልምና መጀመሪው ወር) ኢማም ሁሴንና ጓዶቹ በከርበላ በርሃ የደርሰባቸውን መጣማት ለማሰብ የአርዳቤል ኗሪዎች ታሽት ጎዛረ የተባለ ሀይማኖታዊ ሰኑስርአት ያከናውናሉ።


የዚህ አካበቢ ዘፈን በምስራቅ ካሉ ተዋቂ የዘፈኖች ዝርዝር ውስጥ የሚጠቀስ ነው። ይህ ዘፈንም ማቃሚ ወይም ራዲፍ የሚባል (የሙያተኛ ዘፈን) እና እሺቂ (የሀገረ-ሰብ ዘፈን) የሚባሉ ሁለት ስልቶች አሉት። በአረዳቢል  ያሉ ሴት ዘፋኞች ሳዛንዳ ሲባሉ ወንዶቹ ደግሞ እሺቅሞትሪብ በመባል ይታወቃል።


በአርዳቢ ያሉ የእድ-ጥበባትም፡ ጃጂም ባፈ የሚባለው የሽመና አይነት፣ ሰፌት፣ የአንጥረኛ ሥራ፣ የፈረስ ጫማ ስራ (ሳራጂ)፣ የድንጋይ ጠረባ፣ የአርብቶ አደሮች ቁሳቁስ የሚሰራበት ማፍራሽ በፊ እና የሱፍ ጨርቅ ስራ ናቸው።


የአራዳቢ ነዋሪ ዋነኛ ምግቦች የሚከተሉት ናቸው፡- አሼ ሺር፣ አሼ ዱግ፣ ቀይማቅ (የወተት ክሬም)፣ ቶርሺ ቆርሜህ፣ እሼ ኦማጅ፣ ኣሼ ያርማ (የሰንዴ መረቅ)፣ ቄይሳቫ (የቴምር፣ ወተትና ቅቤ ክሬም) እና ቄይቃናቅ (የፈላ የስኳር ጭማቂ፣ ሳፍሮንና እንቁላል)። የሳባላን የተጣራ ማር  እና ሃልቫዮ ሲያህ (ከዱቄትና ከቅቤ ክሬም የሚሰራ ጣፋጭ) በዚህ አካባቢ የሚዘወተሩ ታወቂ ምግቦች ናቸው።[2]

  1. ^ Cite error: The named reference :1 was invoked but never defined (see the help page).
  2. ^ Cite error: The named reference :0 was invoked but never defined (see the help page).

ቡሼህር[edit]

ቡሼህር ደረቅና ከፊል ደረቃማ በሆነው በኢራን በስተደቡብ ክፍል ትገኛለች። በፐርሽያ ባህረ ሰላጤ እንደ ማሳለጫ አይነት ቅርፅ ያለው በስተሰሜንና በስተምስራቅ የሚገኘው የተራሮች ሰንሰለት ከደላላማ አካባቢዎቹ ጋር ሲደማመር ለአካባቢው የተለያዩ ገፅታ ይሰጠዋል። በስተሰሜን የሚገኘው

ጋች ቶርሽ÷ ከጊስካን፣ ሲያህ እና ኮርሙጅ ከፍተኛ ቦታዎች ጋር በመሆን ዋነኛው የተራራ ሰንሰለት ነው። የቡሼህር የአየር ፀባይ በአብዛኛው ከፊል ሞቃታማ ነው። በጠረፍ አካባቢ ከፍተኛ ሙቀትና እርጥበት ሲኖር በመሀል ሥፍራዎች ደግሞ መለስተኛ የሆነ የሙቀትና የእርጥበት መጠን ይገኛል። የአየሩ ፀባይ በረሃ ቀመስ መሆኑም በአካባቢው ያለውን በእርሻ የተሸፈነ ሥፍራ ዝቅተኛ ሊባል ወደ ሚችል ወደ 3 በመቶ ያነሰ እንዲሆን አድርጎታል። በዚህ አካባቢ የሚገኘው ውስን ደን እንደ እስኮፓርያ፣ ዋይልድ ፒስታኪዮ፣ ታማሪስክ እና ዙዚፋስ ያሉ ዛፎችንና አልፎ አልፎ የሚታዩ ቁጥቋጦዎችን የያዘ ነው። ሆኖም በፐርሺያ ባህረ ሰላጤ ዳርቻ ላይ አልፎ አልፎ የሚታዩት የሀራ እና የማንግሮቭ ደኖች ለአካባቢው ጥሩ ገፅታን አጎናፅፈውታሉ። እነዚህ ደኖች ለባህር ኤሊዎችና ለድንበር የለሽ ወፎች መኖሪያ ሲሆን ለሌሎች ደግሞ የመፈልፈያቸው ቦታ ነው። የዛፍ ላይ አትክልት የሆኑት ቦትሪ፣ መንደሪን እና ሎሚ በዚህ ደን ውስጥ አልፎ ይስተዋላሉ። ከ10 ሚሊዮን በላይ የቴምር ዛፎች ያሏት የቢሼህር ግዛት ከኢራን አንደኛ የቴምር አምራች ነች። እንዲሁም ይህ አካባቢ ድንጋያማ ባህሪ ያለው ስፍራው ከፐርሺህ ባህረ ሰላጤ ጋር በሰፊው ይዋሰናል። ቡሼህር ቋሚም ወቅታዊም የሆኑ ወንዞች አሏት። ከቋሚ ወንዞች መካከልም ሞንድ አንደኛው ሲሆን ብዙ ውሃን በማፍሰስ ቀዳሚውም ነው።


“ቡሼህር” የሚለው ቃል “የአርዳሺር የምህረት ከተማ” የሚል ትርጉም ካለው “ቦክት አርዳሺር” ቃል የመጣ ነው። ቡሼህር ከክርስቶስ ልደት በፊት በ2ኛ ሺህ ጊዜ በነበረችው

የሪሻር ወይም ራሜ አርዳሺር ጥንታዊ ወደብ ፍርስራሽ ላይ የተሰራች ከተማ ነች። አንዳንድ የታሪክ ሰዎች እንደሚናገሩት የሳሳኒድ ኢምፓየር የመጀመሪያው ንጉስ የሆነው አርዳሺሬ ባባካን የጥንቷ የሪሻረ ከተማ መስራች ነበር። በአካሜኒድ ጊዜና ኢራን 30 ግዛቶች በነበሯት ወቅት ቡሼህር የምትገኘው በፓሪስ ግዛት ውስጥ ነበር። ታላቁ ዳሪስ በቀይ ባህር የፐርሺያንና የኦማን ባህረን ከግብፅና ከሚዲትሪንያን አካባቢዎች ጋር የሚያገናኘውንና ከምዕራብ ወደ ምስራቅ የሚያሻግረውን የስዊዝ ቦይ እንዲሰራ ትዕዛዝ በሰጠበት ወቅት የአካሜኒድ ወታደሮች ይህንን ረጅም የባህር መንገድ ለመቆጣጠርና ለመጠበቅ ሲባል በካርክ ደሴት ላይ ሰፍረው ነበር።


በናዴር ሻህ ግዛት ወቅት ቡሼህር ትንሽዬ መንደር ነበረች። በኋላ ላይ ግን የባህር ሀይል ሲሰፍርባትና ትልቅ የወደብ  መድረክ ሲገነባባት ከጐንደር አባስ ወደብ እንኳን በልጣ የኢራን ዋነኛዋ ወደብ መሆን ችላ ነበር። በኢራንና ኢራቅ ጦርነት ወቅት ይህ አካባቢ ግንባር ቀደም የኢኮኖሚና የስትራተጂ ጠቀሜታ ነበረው።


የቡሼህር ዋነኛ መስእብ የሚባለው ማህበራዊ ገፅታው ነው። በአመት ውስጥ ለ7 ወር ከሚኖሩት ቃሽቃዩ ከሚባሉ ማህበረሰቦች ወጪ በቋሚነት እዚህ የሚኖር ጎሳዎች የሉም። በረሃማ አካባቢ ስለሆነ ውሃ በቡሼህር ከፍተኛ ዋጋ አለው። ስለሆነው ለዝናብ የሚባል  የባህላዊ ዘፈንና ስርአት የዚህ አካባቢ ነዋሪዎች መገለጫ ባህላቸው ነው። ከእንደዚህ አይነቱ ስነ-ስርዓት መካከል በ3 ተከታታይ ምሽት የሚከወነውና ቴክቴኩ በመባል የሚታወቀው አንደኛው ነው። በዚህ ስነ-ስርዓት ላይ ሁለት ሰዎች ፊታቸውን ሸፍነውና እቃ ይዘው ወደ ሌላ ሰው ቤት ይሄዳሉ ። ባላባቱ ለነዚህ ሰዎች ስኳር ወይም ሻይ አፍሶ ይሰጣቸዋል። ይህ ስጦታም ለድሆች ይከፋፈላል። የአካባቢው ሰዎች እነዚህን ሦስት ምሽቶች ተከትሎ ዝናብ እንደሚዘንብ ከፍተኛ የሆነ እምነት አላቸው። ጋልጋሊን የሚባለው ደግሞ በቡሼህር የሚከወን ሌላኛው የዝናብ መለማመኛ ሥነ-ስርዓት ነው። በኢኮቴር አካባቢ እንደመገኘታቸው መጠን ድንገተኛ ጎርፍ ስለሚፈሩ ዱቄት በአፋችው ይዘው እዝናቡ ላይ በመትፋት ለፀሀይ የመለማመኛ ስነ-ስርዓት ያከብራሉ። በጣም በሚሞቀውና እርጥበታማ በሚሆኑት በጋዎች ደግሞ ለንፋስ የመለማመኛ ስነ-ስርዓት ያከናውናሉ። በረመዳን ወር ደግሞ ዶምዶም ሳሃሪ የሚባል ስነ-ሰርዓት ይዘጋጃል።በረመዳን ለሊት ሁለት ሰዎች ከበሮ በመምታት ሰዎችን ለሱህር ይቀሰቅሳሉ። በኢድ አል-ፈጥር በዓል ላይም የከበሮ መምታት ስነ-ስርዓት ይከናወናል። በዚህ ጊዜ ግን ከህብረተሰቡ የሚጠብቁት ሽልማት ይኖራል። በቡሼህር የሚደረጉ የሰርግ ስነ-ስርዓቶችም ቢሆኑ የሚገራርሙ ክንውኖች አሏቸው።


በዚህ አካባቢ ብዙ በንፋስ የሚሰሩ የሙዚቃ መሣሪያዎች አሉ። እነዚህ መሳሪያዎችም ሄይ አንባን ፣ኔይጀፍቲ እና ኔይ ታኪ ሲሆኑ ከቆዳ የሚሰሩት ደግሞ ዳማም፣ ታምቡር እና የመሳሰሉት ናቸው። ከእነዚህ የሙዚቃ መሳሪያዎች ዳማም፣ በልንድ የሚሰራውና “ሲምባል”የሚዘወተሩት የሁሴን እና አባቱን የኢማም አሊን መስዋትን ለማሰብ በአሹራ በሚደረጉ የሀዘን ዝግጅት ላይ ነው።


ቡሼህር የምትገኘው በባህር ዳርቻ እንደመሆኑ መጠን እርሻና የከብት እርባታ በብዛት የሉም። በመሆኑም የዚህ አካባቢ ዋነኛ ምግቦች የባህር ምግቦች ናቸው። የሚዘወተረው ምግብ ቃልዬህ የሚባል ሲሆን በተለያየ ቃና ይሰራል። የቃልዬህ አይነቶችም የሚከተሉት ናቸው። ቃልዬህ ማሂ፣ቃልዬህ ሜይጉ፣ ቃልዬህ ኤስፌናጅ፣ ቃልዬህ ባዴምጃን፣ ቃልዬህ ካዱቶርሽ፣ ቃልዬህ ቤሬንጅ እና ቃልዬህ ሀቪጅ ናቸው። ከጣፋጭ ምግቦች ደግሞ ኸሪምፕ ኬባብ፣ አብጉሽት ማሂ፣ “ሽሪኘ” “ስክኒትዜል” ጌምንህ ወይም ሌሌክ፣ ታንዳዝማሂ፣ሆሽቴህ እና የማር ሃልዋ  ናቸው ። ቴምርም በሰፊው ስለሚመረት ለብስኩት መስሪያና እንደ ራንጊናክ፣ ቻንጋል፣ ካራክ ቦክቴህ ላሉ ዳቦች መጋገሪያነት ይጠቅማል። በባንዳሬሪግ በስተምስራቅ በምትገኘው ከሀክ አካባቢ “ቬይን”ን ልዩ በሆነ መልኩ የማረስ ልምድ አለ። በዚህ የአስተራረስ መሰረትም “ቬይን” የሚቀበረው ሁለት ሜትር ጥልቀት ባለው ጉድጓድ ውስጥ ነው። እያደገ ሲሄድ የስሩ ጫፍ ውሃውን ስለሚያገኘው ውሃ ማጠጣት አያስፈልግም።

በቡሼህር የሚታወቁ የእደ-ጥበብ ውጤቶች የሚከተሉት ናቸው፡ ጋቤህ ባፊ፣ የሰአትና፣ የምንጣፍ ስራዎች (በሽመና ጥበብ የሚሰሩ)፣ ጎላ ባቱን ዱዚ እና የሸክላ ስራዎች። ከእንጨት የሚሰራው ጀልባም በዚህ አካባቢ የሚዘወተር ጥበብ ነው።

[1][2]

  1. ^ Cite error: The named reference :0 was invoked but never defined (see the help page).
  2. ^ Cite error: The named reference :1 was invoked but never defined (see the help page).

ጊላን[edit]

ጊላን የምትገኘው በኢራን በስተሰሜን አካባቢ ሲሆን ካስፒያን ባህርና አዜርባይጃዳን በስተሰሜን በኩል ያዋስኗታል። የዚህ አካባቢ መልካአምድር ተራሮች፣ ጉብታዎችና በዳርቻ በሚገኙ ደለሎች የተሞላ ነው። የዚህን አካበቢ የአየር ፀባይ የሚወስኑት የሚገኝበት ከፍታ፣ የአልኮርዝና ታሌሽ የተራራ ሰንሰለቶች አቅጣጫ፣ ለካስፒያን ባህር ያለው ቀርቤታ አና የሰሜኑና የምዕራብቡ የአየር እምቅ ነፋሶች አንቅስቃሴ ናቸው። የአየር ፀባዩም የወይን አደጋ፣ የካስፒያን አየር፣ ነፋሳማና ከፊል ደረቃማ ነው። ከካስፒያን ባህር የሚነሳው እርጥበት አዘል አየር በክረምትና በበጋ ያለውን የአየር ፀባይ ያስተካክላል። ጠቅለል ባለ መልኩ የጊላን የአየር ፀባይ ከሰሜን ወደ ከፍተኛ ቦታዎቹ ወዳሉት ደቡብ ሲኬድ እየቀነሰ ይሄዳል። ሆኖም ግን በዚህ አካባቢ ሀይለኛ ዝናብና በረዶ በተከታታይነት ይከሰታሉ። የዚህ አይነት የአየር ፀባያት መኖርም ጊላንን ከፍተኛ የሆነ የውሃ ሀብት እንዲኖራት አስችሏታል። ለጊላን ውሃ ፍጆታ የሚጠቅመው ውሃ የሚገኘው ከፋማናትና ከሴፈድ ሩድ ወንዞች ነው። ሴፊድ ሩድ ወንዝ ግን በይበልጥ ታዋቂና ዋነኛው ወንዝ ነው። ከባህር አጠገብ ያሉት መለስተኛ ሀይቆች፣ ረግረግ ስፍራዎችና ኮሬዎች (ሳል ) እንደ ውሃ መገኛነት ያገለግላሉ። የውሃ ጉድጓዶችና ምንጮችም ተጨማሪ የውሃ መገኛዎች ናቸው። ደን (አረንጓዴው ወርቅ) ለጊለን የተሰጠ ታላቅ በረከት ነው። አንድ ሦስተኛው ክፍል ማለትም 565 ሺ

ሄክታር የሚያክለው ስፍራ በደን የተሸፈነ ነው። በካስፒያን ባህር አካባቢ ከ20 እስከ 70 ኪ.ሜ የሚደርስ ከፍታ ላይ የሚገኝ ሲሆን ወደ ደቡብ በሚኬድበት ወቅት በአልቦርዝና ታሌሽ አቅራብያ ግን እስከ 2500 ሜ ከፍታ ድረስ ይደርሳል። የደኖቹ አይነትና ብዛት የተለያዩ ናቸው። 224 ሺህ ሄክታር ስፋት ያላቸው ለምለም ስፍራዎች የመሬቱን ለምነት በመጠበቅ እና ለኢንዱስትሪና ለምግብ ፍጆታነት የሚጠቅሙ ምግቦችን በማፍራት ጠቀሜታ አላቸው።


በጊላን ሰዎች መኖር የጀመሩት ከ3000 አመት በፊት ነበር። የዚህ አካባቢ ቀደምት ሰፋሪዎች በታችኛው ደለል ላይ የሰፈሩት ጊሎችና በተራራው ላይ የሰፈሩት ዴላሞች ናቸው። በጊላን ውስጥ የምትገኘው የራሽት መዲና የገነነችው ከስላፋቪድ ጊዜ ጀምሮ ነው። በቃጃር ሥርወ-መንግሥት ጊዜ ደግሞ ራሽት በኢራን ካሉ የንግድ ማዕከላት አንደኛው ነበረች። የዴህኮዳህ መዝገበ ቃላት እንደጠቀሰው “ጊላን” የሚለው ቃል የተገኘው “ጊል” ከሚለው የፓህላቪ ቃል ሲሆን ትርጉሙም “የጊሊቶች አገር” ማለት ነው። ግሪኮች ጊሊቶችን ካዱሲ ይሏቸው ነበር። ዜኖፎኖች ‹ጦር ወዳዶች› ሲሏቸው ማርኩስ አንቱኒዩስ ፓርቲያኖችን ሲወጋ ጎበዝ ጦር ወርዋሪዎችና እግረኛ ተዋጊ ሆኖ እንዳገኛቸው ስትራቦ ዘግቧል።

የሚመቹትና የሚማርኩት የጊለን የአየር ሁኔታዋና ተፈጥሮዋ ብቻ አይደሉም። የጊለን ጎሳዎች አኗኗርም ቀልብን ይስባል። በጊላን ያሉ ጎሳዎች በምዕራብ የሚኖሩት ታሌሾችና በምስራቅ የሚኖሩት ጋሌሾች ተብለው ለሁለት ይከፈላሉ። በዚህ አካባቢ የራሳቸው የሆነ የአኗኗር ሁኔታ፣ አለባበስ አይነትና ባህል ያላቸው ዋነኛ ጎሳዎች የሚከተሉት ናቸው፡- ካሸብሪ/ ካሼባሪ/፣ ሻንዴርማን፣ ማሱሌህና አማርሉ ናቸው። እንዲህ ያሉ የተለያዩ ጎሳዎች መኖራቸውም ይህን አረንጓዴና ለምለም አካባቢ የበለጠ አሳምሮታል።


የጊለን ነዋሪዎች ሰርጋቸውን የሚከውኑበት የራሳቸው የሆነ ባህል አላቸው። ከዚህ በተጨማሪም ኢድ አልፈጥር፣ ኢዳል አድሃ፣ ኖውሩዝና ቲርጋን ያሉ ሃይማኖታዊና ጥንታዊ የሆኑ ባዕላትንም በጣም በደመቀ ሁኔታ ያከብራሉ። ጊሼህ ባሪ የሚባለው ባህል ሙሽራው ሙሽሪትን ከቤቷ በሚወስዳት ወቅት የሚከወን ስርአት ሲሆን ይህም ሳዝና ናቃሬህ የሚባሉ ባህላዊ የሙዚቃ መሳሪያዎችን በሚጫወቱ የባህል ዘፋኞች ጭፈራና ዳንስ የታጀበ ነው። በጊላን በስተምስራቅ ያሉ ነዋሪዎች ደግሞ ሙሽራዋ ከቤተሰቦቿ ቤት ስትወጣ አዲሱ ቤቷ የምትተክለውን ችግኝ ይዛ ነው የምትወጣው።


እዚህ የሚዘፈኑ ባህላዊ ዘፈኖች የአንድነታቸው ነፀብራቅ ሲሆኑ ይዘታቸውም ጀግንነት፣ ሥራ፣ ክብረ በዓል፣ ፍቅር፣ የህፃናት፣ ሀይማኖታዊና ስለ አዲስ አመት የሚያወሱ ናቸው። በዚህ አካበቢ ሌሎች ባህላዊ ዘፈኖችም አሉ። እነዚህም ካሬህ (ካር ላንግ)፣ ባህላዊው የትግል ውድድር ሲደረግ የሚዘፈነው ከሽቷ ማቃም፣ ሙሽሪት ከቤቷ ስትወጣ የሚዘፈነው አሩሲ ባራን፣ በሬዎች ሲዋጉ የሚባለው ቫርዛ ጃንግ፣ ፓህላሺ ካኒ (የጊላኪ ስንኞቹ)፣ በእርሻ ቦታ ላይ የሚዘፈነው ቤጃር ሳሪ፣ የዳሽቲ ዘፈን የሆነው ጌሌን ኬሺ፣ ቫልግሪዚ፣ ሙሽራውሙሽሪትን ሲወስዳት የሚባለው ጄሉኒ፣ የታዋቂው ኢራናዊ ሙዚቃ የሆነው የአቡል ሀሰኔ ሳባ ሙዚቃ ዛራማሊጄህ፣ የጊላን ምስራቃዊ አካባቢ ነዋሪዎች ጥንታዊ ሙዚቃ የሆነው ለናይ ሙዚቃ ናቸው። ታዋቂዎች ባህላዊ የሙዚቃ መሣሪያዎች ደግሞ ኮርኒ፣ ፒፔ፣ ሶርና፣ ዋሽንት፣ ዶምቡክ፣ ዳምቤል፣ ባሊ ቡም፣ ዳይሬህ፣ ዳይሬህ ዘንጊ፣ ‹‹ሲምባልስ››፣ ሳንቱር፣ ጋቭ ጉራኔህ፣ ሻት፣ ዶታሬ ታሌሽንና ጊሌህታር ናቸው።


የኢራን ጣፋጭ ምግቦች በአብዛኛው በጊላንም ይገኛሉ። ቱሪስቶች የእነዚህን ትሁት ሰዎች ምግቦች ሊቀምሷቸው ይገባል። እነዚህ ምግቦች የሚዘጋጁት ከሩዝ፣ ከትኩስ ጎመኖችና አታክልት ነው። ስብ ከሌለው ስጋ የሚሰራው ኩትካ፣ በቄላ ቃቶቅ፣ ሴጃን፣ ሞርግ ቶርሽ፣ ቶርሺ ታሬህ፣ ሚርዛ ቃሴሚ፣ ሲር ቃልዬህ፣ ‹‹ካቪር›› እና በአሳ የሚሰሩ የተለያዩ ኬባቦች ጣፋጭም ምግቦች  ናቸው። ኪሉቼህ የሚባለውን እነደ ኩኪስ አይነት ምግብ ቱሪስቶች ብዙ ጊዜ ገዝተው ወደ ሀገራቸው ይወስዱታል። በኢራን ሰሜናዊ አካባቢ በቂና ትኩስ የአትክልት ውጤቶች ስለሚገኙ የተለያዩ የምግብ አይነቶነችና ጭማቂዎች እንዲኖሩ አስችሏል።


ከጊላን የእደ ጥበብ ውጤቶች መካከል፡- የምንጣፍ ሽመና፣ ሞርቫር ባፊ፣ ኬይዛራን ባፊ፣ የሸክላ ስራ፣ የሀር ስራ፣ ኪሊም እና ጃጂም ባፊ፣ ቻሙሽ ዱጊ፣ የእንጨት ጠረባ፣ ቅብ፣ ቻዱር እና ሻብ ባፊ። ከጥንት ጀምሮ ከሌሎች ኢንዱስትሪዎች በተጨማሪ  የሀር ማምረት ተግባር ታዋቂ ነው። በይበልጥ ደግሞ ይህ ሥራ በሳፋቪድ ጊዜ በራሽት ከተማ ዙሪያ አብቦ የነበረ ሲሆን በኋላ ላይም ኢራን ወደ ውጭ ከምትልካቸው ምርቶች መካከል አንዱ መሆን ችሏል። በሩድባር የማርሊክ ጥንታዊ ተራራ አካባቢ የተገኙት እቃዎች እንዳረጋገጡት የጊላን ነዋሪዎች የአንገትና ጆሮ ጌጣጌጦን እንዲሁም አልባሳትን በመጠቀምና በመጥለፍ ቀደምቶቹ ናቸው።[1]

  1. ^ Cite error: The named reference :0 was invoked but never defined (see the help page).

ኤስፋሃን[edit]

ኤስፋሃን “የአለም እኩሌታ” በመባል ትታወቅ የነበረ ሲሆን የምትገኘውም በኢራን መካከለኛ ስፍራ ነው።  ያላት የአየር ፀባይም መካከለኛና ደረቅ የሚባል ነው። የማርካዚ ተራራ ስንሰለት አካል የሆነው የካረካስ ከፍተኛ ቦታ የሚገኘው በዚህ አካባቢ ነው። በዚህ አካባቢ የሚገኘው አብዛኛው የደለል ስፍራ ሊፈጠር  የቻለው የዛያንዴህ  ወንዝ መዳረሻው ወደ ሆነው ጋቭኩኒ ሲፈስ ነው። 100‚000 ሄክታር የሚሆነው መሬት በደን የተሸፈነ ሲሆን 5‚100 የሚሆነው ደግሞ በተክል የተሸፈነ ነው። ምንም እንኳ የዛያንዴህ ሩድ ወንዝ ያለ ቢሆንም ኤስፋሃን አነስተኛ የውሃ ሀብት ነው ያላት። ይህ ወንዝ የቻሃርማሃል ቫ ባክቲያሪ አጎራባች ከሆነው የኩራህራንግ አካበቢ ከዛርድ ኩህ ተራራማ ስፍራ መገኛ የሚመነጭ ነው። የዚህ የወንዝ ክፍል ውሃ ለስለሚገኝበትም ዛያንዴህ ሩድ “ውሃ የሚያመነጭ ወንዝ ” በመባል ይታወቃል።

ኤስፋሃን በ2006 ላይ የሙስሊሙ  ዓለም የባህል መዲና ተብላ ተሰይማለች። ይህች ጥንታዊት ከተማ በተለያዩ ስሞች ትታወቅ ነበር። ባለፋት ክፍለ ዘመናት ስፓዳንና ስፓሃን ትባል ነበር። በጥንታዊው የፐርሺያ ቋንቋ “ስፓዳና” ማለት ወታደሮች ማለት ነው።  በኋላ ላይ አረበኛ ባሳዳረው ተፅፅኖ ምክንያት ግን ስሟ ኤስፋህን ተባለ። በ1591  ደግሞ የሳፋቪድ ስርወ-መንግስት ንጉስ የሆነው ሻህ አባስ፤ ኤስፋሃን መቀመጫው መሆኗን አወጀ። የኤሰፋሃንን ሀውልቶች ስንመለከት አለም ላይ ካሉ ማለትም በቤጂንግ፣ በፓሪስ፣ በቪንቼና በሮም ካሉት ጋር የሚስተካከሉ የቱሪስት መስእቦች ናቸው።[1]

  1. ^ Cite error: The named reference :1 was invoked but never defined (see the help page).

ጎሌስታን[edit]

ጎሌስታን በኢራን በስተሰሜን ምስራቅ የሚገኝ ሲሆን በስተሰሜን በኩልም ከቱርኬ ሚኒስታን ጋር ይዋሰናል። ጎሌስታን በሚከተሉት ምክንያቶች የተለያዩ የአየር ፀባያት አሏት፡- እነዚህም ጎልስታን የምትገኝበት ላቲቲየድና ከፍታ፣ የአልቦሮዝ ተራራ መገኛ አቅጣጫ፣ ለባህር ያላት ቀረቤታ፣ አካበብያዊና ውጫዊ የሆኑ ንፋሶች፣ በቱርኬሚኒስታን በስተደቡ የሚገኘው በርሃማ ስፍራ እና ሰፊ የደን ሽፋን ናቸው። የዚህ አካባቢ የአየር ሁኔታ ከካስፒያን መጠነኛ እርጥበታማነት እስከ ከፈል በርሃማነት ድረስ የሚለዋወጥ ነው። ይህ ሁኔታም ጎሌስታን በኢራን ካሉ ለምለማማ ቦታዎች አንደኛዋ እንድትሆን አስችሏታል። የአየሩ ፀባይ፣ የመሬቱ ሁኔታ እና ለባህር ያላት ቅርበት ጎሌስታን ሰፊ የውሃ ሀብት እንዲኖራት አስችሏታል። እዚህ ከ40 የሚበልጡ ወንዞች ሲኖሩ አትራክ፣ ጎርጋንሩድ፣ ቃልህሱ፣ አቤጀ ዞሊ፣ አንጂላብ፣ አቤቼል ቼሊ እና ቼናሽግ ተጠቃሾቹ ናቸው። እንዲሁም 140 ያህል የሚሆኑ ትናንሽና ትላልቅ ምንጮች ተጨማሪ ውሃ መገኛዎች ናቸው። እነ ፒር ጌር ዴህ፣ ጋቭ ኮሻን፣ ታል አንባር፣ ሃላላን እና ጃሃን ናማ ተራሮች የጎሌስታንን የውሃ ሀብትና የአየር ፀባይ በመጠበቅ ሰፊ ሚና አላቸው።


የዚህ ግዛት መልካአምድራዊ ገፅታ ብዛት ያላቸው ኮሬዎችን የያዘ ተራራማ እና በደለል የተሞላ ዝቅተኛ ሥፍራን የያዘ ነው። የተለያዩ ዝርያ ያላቸው እፅዋቶችና የካስፒን ደን በጎሌስታን በስፋት የሚገኙ ተክሎች ናቸው። ‹‹አክ›› ፣ ቢች፣ ‹‹ዜልኮቫ››፣ ግራርና ‹‹ታማሪስክ›› ዛፎች እንዲሁም ከተክሎች ደግሞ ‹‹በሬጅ››፣ ‹‹ሆሊሁክ››፣ ‹‹ባዮሴት››፣ ‹‹ቤርጋሞት›› ፣ ‹‹ታይም››፣ ‹‹ፊክስዊድ››፣ ‹‹ትረገካንዝ›› እና ሃርማል ለእንስሳት ምግብነት እና ለመድሃኒት መቀመምያነት የሚጠቅሙ በዚህ ግዛት ይገኛሉ።  ይህ ሁሉ ጎሌስታንን በአረንጓዴ የተነጠፈች ምድር አድርጓታል። ጎሌስታን በሳሳኒድ ሥርወ-መንግስት ጊዜ የጥንቱ አካሜኒድ እና የታላቁ ኮራሳን ክልል አካል ነበረች። በእስልምና የመጀመሪያ ዘመናትም ይሁን ከዚህ በፊት ጊሌስታን በሰሜን ኢራን ካሉ ታላላቅና ስልጡን ከተሞች አንዷ ነበረች። ክ13ኛው ክ.ዘ. በፊት ይህ አካባቢ ጎርጋን (ጎርጃን) ይባል የነበረ ሲሆን በ13ኛ ክ.ዘ መካከል ደግሞ አስታርና አበድበል ይባኝ ነበር። ከዚህ በኋላ ግን ጥቁርና ነጭ ሉል የሚገኝበት አረንጓዴውና ለምለሙ ስፍራ ጎሌስታን (የአበባ መገኛ) ይባል ጀመር። ይህ ግዛት የተለያዩ የቱርኪምስታን ጎሳዎች መኖሪያ ስፍራ ነው። (እነዚህ ጎሳዎች በቱርኬምኒተን የሚኖሩት ህዝቦች አካል ናቸው)።


በጎሌስታን የተለያዩ ጎሳዎች ይኖራሉ። ሆኖም ግን በተለይ የታላቁ ቶርካማን (ቱርክሜን) ጎሳ በሰሜን የጎሌስታን አካበቢ መስፈራቸው ለአካባቢው የተለየና ያማረ ማህበራዊ መልክ ሰጥቶታል። ቱርክሜኖች የሚማርክ አንድነት ያላቸው ሲሆን ለጎሳቸው ውሳኔዎችም ተገዢዎችና በስራቸውም ኦውንሊቅ የሚባሉ ንዑስ ጎሳዎች ይገኛሉ። ኦውንሊቅ ደግሞ በተራው የተለያዩ የንዑስ-ንዑስ ጎሳዎች ያሉትን ‹‹ኦውባን›› የያዘ ሲሆን ኦውባም ‹‹አይ›› የሚባሉ በሥሩ አሉ።


ለቱርክሜኖች ከሰርግ ውጪ ሁሉም ክብረ በአላት ሀይማኖታዊ ገፅታዎች አሏቸው። እነዚህን ክብረ-በዓላት ባይራም ሲሏቸው፤ ኢድል ፈጥን ‹‹አራዝ ባይራም›› ይሉታል። በሶፈር ወር የመጨረሻው ረቡዕ ላይ ቱርክሜኖች ቃራህ ቻሃርሻንቤህ (ጥቁሩ ረቡዕ) የሚባል በአይነቱ ልዩ የሆነ የሀዘን ስነ-ስርዓት ይከወናሉ። በቱርክሜኖች ዘንድ አንዱ ጎሳ ሌላው ጎሳ የማግባት ልምድ አላቸው። የመተጫጨቱ ስነ-ስዓት ከተከናወነ በኋላ፤ የሙሽራውና የሙሽሪት ቤተሰቦች በጉጉት የሚጠብቀውን የሰርጉን እለት ለመወሰን ካንካሽ የሚባል ስነ-ስርዓት ይከወናሉ። የሰርጉ ዕለት ለተከታታይ ሦስት ቀናት እና ምሽት ይቆያል።

ጎሌስታኖች የሚያዘወትሯቸው ምግቦች ቼክዴርሜህ እና ሃሊእሸ ናቸው። እንደ በድሬ ቶርካማን ያሉ በካስፒን ባህር በስተምስቅ በሚገኙ ሥፍራዎች ‹ካቪያር›› የሚባለውን አሳ ማጥመድ የተለመደ ነው።


በዚህ አካባቢ የሚገኘው ባህላዊ ሙዚቃ ከኡዛንሶች ጋር የሚዛመድ ነው። ኡዛንሶች እንደሚታወቀው ከምዕራብ ቻይና እና ከደቡብ ሞንጎሊያ አካባቢ ወደ መካከለኛው ኤስያ ከፍለሱት ህዝቦች ጋር የሚዛመዱ ናቸው። ኡዛንሶች ሙዚቃቸውን ለህክምናነትም ይጠቀሙበት ነበር። ዘፈኖቻቸው ጀግኖቻቸውን የሚያውድሱና በጎሳቸው ውስጥና በአለም ላይ ያለን ሀዘንና ደስታንም የሚዳስሱ ናቸው። ዘፈኖቹ ቀለል ባሉ ቃላትና ዜማ የሚዘጋጁ ናቸው። እነዚህ ማራኪ ዜማዎች ከትውልድ ውደ ትውልድ ተላልፈው እስከሁን ድረስ ይገኛሉ። እነዚህን ዜማዎች የሚፈጥሩት እንደ ታምዴሬሀ ፣ ካማንቼ እና ዛንቡራቅ ያሉ ባህላዊ ሙዚቃ መሳሪዎች ናቸው።

ምንጣፍ፣ የቱርክሜን ትራሶች፣ የተራራ ጃጂም፣ የሀር ፈተላ፣ ጥልፍ እና ስፌት የጎሌስታን ሰዎች ጥበቦች ናቸው። በወርቅ፣ ብር እና በሌሎች ውድ የሆነ ማዕድናትን በመጠቀም ጌጣጌጦችን የመስራቱ ጥበብ ቱርክሚኖች በጣም የተካኑበት ሥራ ነው።[1]

  1. ^ Cite error: The named reference :0 was invoked but never defined (see the help page).

    ሃሜዳን  [edit]

ሃሜዳን የምትገኘው በኢራን በስተደቡብ ክፍል ሲሆን ከሀገሪቱ ቀዝቃዛ አካባቢዎች አንዷ ናት። የዚህን ሥፍራ አየር ፀባይ የሜድትራንያን ምዕራባዊ ንፋስ፣ ከሰሜን  ምዕራብ የሚነፍሱ ሌሎች ንፋሶች፣ ጥቁር ባህርና ከአውሮፓ የሚነፍሰው የሰሜን አካባቢ አየር ይወስኑታል። እርጥበታማና ዝናብ አዘል የሆነው ንፋስ በመልክአ ምድራዊው ፀባይ እና አካባቢው በከፍተኛ ሥፍራ ላይ ስለሚገኝ አብዛኛውን እርጥበቱን ያጣል። በአጠቃላይ ሲታይ የዚህ አካባቢ የአየር ሁኔታ ወይና ደጋማ ነው ሊባል ይችላል። የአልቫንድ ተራራ በሃሜዳን  ሰንሰለት ትልቁ ነው። እንዲሁም ጋርሜህ፣ ሴድሬህ፣ አላቦለግ፣ ጋሩ (ጋሪ)፣ ቡቃቲ እና ካን ጎርማዝ ከፍታዎችም ተጠቃሾች ናቸው። በሃሜዳን ያሉ አብዛኞቹ ተራሮች እርጉዱ ለተራራ እስፓረት መሰሪነት አመቺዎች ናቸው። በአንፃሩ ሰፊ የሆነ ሜዳማና ለምለም የሆነ ደለላማ ሰፍራዎች ስለሚገኙ እንደ ስንዴ ያሉ ጥራጥሬዎችን ለማምረቻ ተስማሚ ነው። እነዚህ ሜዳማ ሥፍራዎችም ናቸው የጠነከረ  ንፋስ እንዲኖር ያስቻሉትና ሃሜድንም ልዩ ንፋሳማ አካባቢ ያደረጋት።  በስተሰሜን ምስራቅ የሚገኙት የካቪርጃን፣ ራዛንና አቫጅ ሰፈና ሜዳማ ሥፍራዎች የሃሜዳን ተጠቃሾቹ ዝቅተኛና ለምለም ሥፍራዎች ናቸው። በቀደመው ጊዜ የሃሜዳን ብዙው ቦታ በደን ተሸፍኖ የነበረ ቢሆንም አሁን ግን የናሃቫንድ ከተማ የተወሰነ ክፍል ብቻ ነው ደን ያለው። ኦክ የሚባለው የዛፍ አይነት ታዋቂ ነው። በተጨማሪም ‹‹በራጅ››፣ ሊኮሪቴ››‹‹ታይሙስ ቩልጋሪስ››‹‹ፊክሽሽክድ››‹‹ትራጋካንስ››‹‹ዋይልድ ፔስታኪዮ›› እና ‹‹ኣዛሮሌ›› እንዲሁ በስፋት የሚገኙ የዛፍ አይነቶች ናቸው። የዚህ አካባቢ የውሃ መገኛ ምንጮች ጋማሊያብ፣ ቃራህቻይ እና ታልቫር የሚባሉት በመሬት  ላይ ያሉትና በአሳድ አባድ እና በናሃቫንድ ዝቅተኛ ቦታዎች ያሉት ምንጮችና ኩሬዎች ናቸው።


የኤክበታን እና የአብሺናህ ግድቦችም ለሃሜዳን ከተማ ነዋሪዎች የመጠጥ ወሃ መገኛ ሲሆኑ አልፎ-አልፎም ለእርሻ ማልሚያነት ያገለግላሉ። የኣሲርያን ንጉስ የሆነው ቀዳማዊው ቲግላስ ፒሌሴር (1000 BC ) መረጃ እንደሚያስረዳው የሃሜዳን ስም ‹‹አማዳያ›› ነበር። እንደ 5ኛው ክ.ዘ (BC) የታሪክ ሰው ሄሮዱቶስ እምነት የኤክባታና (የአሁኗ ሃሜዳን) የተቆረቆረችው የሜዴስ የመጀመሪያ ንጉስ በሆነው ዲጴቼስ ጊዜ ነበር። በጥንቱ ፕርሺያ ቋንቋ ሃሜዳን የምትጠራው ‹‹ሃግማታና›› (የስብሰባ ስፍራ) ነበር ። እንደ ሄሮዱቶስ እምነት ኤክባታና (ሃግማታና) የሜዲያን ኢምፓየር መቀመጫ ነበረች። በአንድ ክፍለ ዘመን ጊዜ ውስጥ ግን ሃግማታና በአካሜኒዶች ቁጥጥር ስር ውላ ከእነርሱ ከተሞች አንዷ አደረጓት። እንደ ታሪክ ተመራማሪዎች የአካሜኒድ ንጉሶች ቅርሶች እዚህ ይገኛል።


ለምሳሌ በኮረብታ አካባቢ ተቆፍሮ የተገኘው መረጃ እንደጠቆመው በፓረሲን ሥርው-መንግስት ዘመን ሃሜደን የወታደር ምሽግ ነበር። የሳሳኒድ ወታደሮች ይህ ቦታ ለቲስፍንና ሹ ቀረቤታ ያለው በመሆኑ በበጋ የሚያርፉበትን ቤተ-መንግስት ሰርተው ነበር። ሃሜዳን በኬይላሚያን መሪዎች ዘመን አድገቷ ቆርቁዞ ነበር። ከጥቂት ጊዜ በኋላ ግን ማንሰራራት ችላ የሴልጁካ ሥረወ-መንግስት መአከል ሆነች። በሳፋቪድ ጊዜ ደግሞ ሃሜደን የበለጠ ተሸሽላ በቃጃር ሥርወ-መንግስት እጅግ ጠቃሚና ሀብታም ግዛት መሆን ቻለች።


የሃሜዳን ተራራማ አካባቢና የተለያየ አየር ፀባይ መኖሩ ለተጓዦቹ ጎሳዎች በተለያየ ጊዜያት አመቺ የመስፈሪያ ቦታ ሆኗቸዋል። ይህም አካበቢው የተለያየ መስህቦች እንዲኖሩት አስችሏል። እዚህ ያሉት ዋናዎች ጎሳዎችም የሚከተሉት ናቸው፡- ቶርካሽቫንድ፣ ጀሚር፣ ታሬምታቅሉ እና ባናፍሼህጾ። በተጨማሪም ከኬርማንሻህ ግዛት የሚነሱት የኢላም፣ ሎሬስታን እና ማርካጊ ጎሳዎችና ቤተሰቦቻቸው በበጋ ጊዜ በሃሜዳን ተራሮች ላይ ይሰፍራሉ።


በእነዚህ ህዝቦችና በሃሜዳን ነዋሪዎች የሚከወኑ በጣም አስደሳች የሆኑ ባህላዊ ስርዓቶች አሉ። ከእነዚህ ሥርአት መካከልም ሻቤ ያልዳ  (ሻቤ ቼሌ ቦዞርግ)፣ ቼሌዮ ኩንቻክ፣ ቻህርሻ ንቤህሱሪ፣ አራፌህ  እና ሳማኑ ፓዛን ተጠቃሾ ናቸው። ሺርሻሬህ የሚባለው ክንውን፤ ከከብቶች የሚገኘው ምርት እጥረት በሚኖርበት ወቅት ያላቸው ለመከፋፈል የሚደረግ ነው። በበጋ ወቅት ከሚከወኑት መካከል የእህል መውቂያ ስነ-ስርአት አንደኛው ነው። ፓዩቫኔህ ሌላኛው ጥንታዊ ክብረ በዓል ሲሆን የሚከወነውም በክረምት ጊዜ ሆኖ በቤተሰቡ ቁጥር ልክም ዶር ይጠበሳል። የበለጠ ፀጋንና በረካን ከዝናቡ ለማግኘት በማሰብ ኮም ኮሜህ ካቱነ፣ ጋበቭባር፣ ህኸሊ እና ኩሴህ ጋርዲ (ኩሴሀ ጋሊን) የሚባሉ የዝናብ ክብረ-በዓል ይዘጋጃል። በአዲሱ አመት ዋዜማ ላይ ወጣቶች የልብስ ሰቀላ (ሻል ዶርኪ) ስነ-ስርዓት ይከናውናሉ። ይህ ለማድረግም ወደ ጎረቤታቸው ጣራ ላይ ይወጡና ረጅም ለብስ ቤቱ ላይ አንጠልጥለው የአዲሱን አመት መግባትን በመናፈቅ ይዘፍናሉ። ምንም እንኳን የሃሜደን ነዋሪዎች የራሳቸው የሆነ ባህላዊ ዘፈን ባይኖራቸውም እንደ ኩርዶ፣ ቱርኮችና ሉሮ ሉጎሳዎች በተሰረቅራቂ ድምፃቸው የሚዘፍኑና የሚደንሱ ስለሆነ ይህም የአካባቢውን መስዕብነት ይጨምረዋል።


በሃሜዳን  የተለያዩ የምግብ አይነቶች ይዘወተራሉ። እነዚህም እሼ አማጅ፣ አሼ ሳር ኩሌህ፣ አሼ ታማሺ፣ ቦሩሽ አቡጉሽቴ ቤህ፣ አብጉሽቴ ካላም፣ ሬዝ ኬባብ፣ ኩሬዮ ኬባብ፣ ሃሜዳኒ ኩፍቴህ አና ሃሊም፣ ኩኩዬ ፓኒር እና ኮሬሼ ጎወጄህ ሳብዝ ናቸው። የተለያዩ ጭማቂዎች፣ ሊቴህ እና ፌልፌል እንዲሁም እንደ ባርሳቅ፣ ሱጁቅ፣ የማር ባስሉቅ፣ ፒኬህቹክ እና ናርጂሊ ያለ ብስኩቶች ከዋና ምግብ ጋር አብረው ይቀርባሉ።


የምንጣፍ ሥራ በሃሜዳን  የተለመደ ሥራ ነው። የቆዳ ውጤቶችም ከጥንት ጀምሮ ከፍተኛ ጥራት አላቸው። የጥልፍ ሥራ፣ የሸክላ ሥራ፣ የሴራሚክ ስራ፣ ጊቬህ ባፊ፣ የጫማ ስራ፣ ፑስቲን ዱዚ እና የቆዳ መፋቅ ስራዎች በሃሜዳን የሚታወቁ ጥበቦች ናቸው።

ሆሮሞዝጋን[edit]

ሆርሞዝጋን በኢራን በስተደቡብ የምትገኝ ሲሆን ከፐርሽያ ባህረ-ሰላጤ እና ከኦማን ባህር  በስተሰሜን ትገኛለች። በጣም ተራራማ ስፍራ ስትሆን በስተደቡብ በኩል እንደ ዛርጎን ያሉ ከፍተኛ የተራራ ሰንሰለት አሏት። ፋርጋገን፣ ሻብ (ሾ) እና ጌኑ የሚባሉም ከፍተኛ ስፍራዎችን ይዛለች። ከተራራማ ቦታዎች በተጨማሪም እንደ ጋቭባንዲና ማራግ ያሉ ሜዳማ ቦታዎች፤ እንደ ሚናብ እና ባንዳር አባስ ያሉ የባህር ዳርቻ ደላሎች እና በፐርሺያ ባህረ ሰላጤ ውስጥ የሚገኙ ብዙ ደሴቶች በሆርሞዝጋን ይገኛሉ። የዚህ አካባቢ ደሴቶች ሦስት አይነት መልክ አላቸው። አንደኛው እንደ ቄሽም ያሉ በዛግሮስ የተራራ ሰንሰለት ላይ የሚገኙ፤ ሁለተኛ እንደ አቡሙሳና ኪሽ ያሉ ከባህር ቅሪቶች የተፈጠሩ፤ ሦስተኛ እንደ ሆርሞዝ ያሉ በጨው ክምችት ላይ የተፈጠሩ። ሆርሞዝጋን የምትገኘው በዋናው ሞቃታማ አካባቢ በመሆኑ በክረምት ጊዜ ለአጭር ጊዜ ከሚታየው ቅዝቃዜ ውጪ አመቱ በአብዛኛው እጅግ ሞቃተማ ነው። ዝቅተኛና ወቅቱን የማይጠብቅ የዝናብ ስርጭት፣ ከፍተኛ የሆነ የትነት መጠን፣ አናሳ የሆነ ተክል እና የሰው ሰራሽ ተፅዕኖዎች ተደምረው ይህ አካባቢ በርሃማ እንዲሆን አስችለዋል። ምንም አንኴን የተክል ሽፋን እምብዛም ቢሆንም በፐርሺ ባህረ ሰላጤና በኦማን ባህር ዳርቻ የሚገኙት የሆርሞዝጋን አካባቢዎች ደኖች አሏቸው። እነዚህ ደኖች ሦስት አይነቶች ናቸው። እነርሱም በተራራ ላይ የሚገኙ፣ በባህር ዳርቻ የሚገኙና በወንዝ ውስጥ የሚበቅሉ ናቸው። የግጦሽ ቦታዎች የአካባቢውን 1/3ኛ የሚይዙ ሲሆን በተለይም በዶራጋ፣ ፋርጋን እና ተሮምና አህማዲ አካባቢዎች ይበዛሉ። ለትሮፒካል ካንሰር በጣም የቀረበ ቦታም በመሆኑ በጣም ሞቃታማ እና አነስተኛ የዝናብ መጠን አለው። በመሆኑም የሆርሞዝጋን የውሃ ከመሬት ላይና ከመሬት ሥር የሚገኝ ውሃ ነው። እነ ሚናብ፣ ጋንጅ እና ጃጊን የሚጠጡ ውሃ መገኛ ወንዞች ሲሆኑ እነ ኮልና ሜህራን ደግሞ ጨዋማ ወንዞች ናቸው።[1]

ኢላም[edit]

ኢላም የምትገኘው በኢራን በስተምዕራብ አቅጣጫ ሲሆን ከኢራቅ ጋር በስተምዕራብ በኩል ትዋስናለች። የኢላም ደቡባዊና ምዕራባዊ ሥፍራ ከፊል በረሃማና ሞቃት ሲሆን ወደ ዝቅተኛውና ወደ ድንበር በሚኬድበት ጊዘ ግን አየሩ ወደ ሙሉ በርሃማና ሞቃታማነት ይቀየራል። የዚህ አካባቢ ተራሮች በስተሰሜንና ሰሜን ምሥራቅ አካባቢዎች የተሰበሰቡ ናቸው። ከነዚህ ተራሮች መካከል ጉዙፎቹ 3,062 ሜ ከፍት ያለው ካቢር ኩህ እና 1,995 ሜ ከፍታ ያለው ዲናር ኩህ ናቸው። በኳተርናሪ ጊዜ የፐርሺያ ባህረ ሰላጤ ውሃ ወደ በኋላ ሲመለስ የድንጋይ መሸርሸር፣ የወንዝ ጎርፍ መከሰት እና የሜህራን፣ ሞህሴን አባድ፣ የዴህሎራንና የዳሽት ደለሎች ተሸርሽረዋል። ተራሮች በኢላም በመገኘታቸው ምክንያት የተለያዩ ተክሎች እንዲኖሩት አስችሏቸዋል። 500,000 ሄክታር የሚሆነው በደን የተሸፈነው ሥፍራ እና የኦክ፣ የዱር ‹‹ፒስታኪዮና›› አዛሮሌ›› ዛፎች የሚገኙት በርሃማና ከፊል በርሃማ በሆነው የዛግሮስ ተራሮች ስንሰለት አካባቢ ነው። ተራሮችና የተለያዩ ተክሎች መኖራቸው ኢላም የከርሰ ምድርም ሆነ በመሬት ላይ የሚኖር ውሃ ሀብት እንዲኖሩት አስችሏታል። ከእነዚህ የውሃ ሀብቶች ውስጥም የጎልጎሌ ማሌክሻሂ ምንጭ ዋነኛው ነው። የዚህ አካባቢ የአየር ፀባይ የተለያየ አይነት ነው። የግጦሽ አካባቢዎች ቀዝቃዛ፣ ወይናደጋና ሞቃት (ቄሽሎቅ) የአየር ፀባያት አሏቸው። እዚህ አካባቢ የሚገኝ አሸዋ 80,000 ሄክታር መሬትን ይሸፍናል። በኢን ከሸቫ አቡ ጎቬይር እና ከኢራቅና ኩዜስታን ጋር በሚዋሰነው ዳርቻ ሥፍራ በነፋስ የተሸረሸረ ቦታ ተገኝቷል። አሁን ኢላም የምትባለው የጥንቱ ኤላሚቴ ኢምፓየር አካል ነበረች። ‹‹ኤላም›› የሚለው ስያሜ ‹‹አይላም›› ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን ግሪክ ደግሞ ከሄብሪው የተወሳው ቃል ነው። ኤላሚቶች ሀገራቸውን ‹‹ሀልታምቲ (ሃታምቲ)›› ብለው ነው የሚጠሩት፤ ትርጉሙም ውድ ሀገር ማለት ነው። በአካድያንና በሱሜሪውያን ደግሞ ከፍያለ ማለት ነው። ሆኖም ግን አርያ- ኖች ከመፍለሳቸው በፊት በአርኪኦሎጂ እንደተረጋገጠው ይህ አካባቢ በከፍተኛው የኢራን ክፍል የሚኖሩት ኢራኖች የሚኖሩበት አካባቢ ነበር። በሳሳኒ ሥርወ-መንግስት ወቅት ኢላም የፓህሌህ ወይም የፓህሉ ምደር አካል ነበረች። ከ10ኛው እስከ 12ኛው ክ.ዘ ባለው ጊዜ ኢላም አረብ ያልሆነው የአራቅ አካል ነበረች፤ አረቦችም ‹‹ጆጃቦል›› (ተራራ) ሲሉ ይጠሯት ነበር። በዚህ የተለያዩ የአየር ፀባያት በሚገኙበት አካባቢ ዋነኞቹ የኩንድ፣ ሎርስ እና አረብ ጎሳዎች በሰላምና በፍቅር ይኖራሉ።

የኢላም ከፍተኛ ተራሮች በክረምትና በበጋ ወቅቶች ለማረፊያነት ከሚያገለግል ለምላማ ሜዳ አጠገብ መገኘታቸው፤ ኢላም ለተለያዩ ጎሳዎች አመቺ ቦታ እንድትሆን አድርጓታል። ባሪናህ የሚባል ስነ-ስርዓት በዚህ አካባቢ ያለ ሲሆን ይህም የበጎች ፀጉርን ልዩ በሆነና ቺያህሬግ በሚባል መቀስ የሚቆረጥበት ዘዴ ነው። በኩርዲሾች ፀደይ ወቅት (በፌብሩአሪ 9) ወጣቶች የሚከወኑት ሌላኛው ባህላዊ ስነ-ስርዓት ነው። በዚህ ክንውን ወጣቶች ወደ ሰው ቤት ደጃፍ ይሄዱና ‹‹ሼሌሀ ሜሌህ›› እያሉ በማዜም ስንዴ፣ ፍራፍሬና ቴምር አስከሚሰጣቸው ድረስ ይዘፍናሉ። ይህ ዘፈን በግዛቱ የረጅም ጊዜ ታሪክ አለው። ቻማር ታዋቂ የጎሳ መሪ ወይም ታዋቂ ሰው ሲሞት ቻማርጋህ በሚባል ስፍራ የሚከወን የሀዘን ስነ-ስርአት ነው። በጋብቻ ወቅትም ቢሆን የተለያዩ ዘፈኖችና ዳንሶች ይገኛሉ። በግልና በቡድን የሚጨፍረው ቹቢ የሚባለው  ዘፈን በኢላም አካባቢ እጅግ ተወዳጅ ነው። የኢላም ሰዎች የሚታወቁባቸው የምግብ አይነቶች ናኔ ሳጂ፣ ናኔ ፓፓጅ፣ ናኔ ፋቲር፣ አሼ ታሪኪኔህ፣ እሼ ሬሽቴ፣ ማስሻ፣ ፔርሼካህ እና በርሳቅ ናቸው።


የሀር ሥራ፣ የቼሌህ ዱኪ ምንጣፍ፣ ኪሊም፣ ሲያህ ቻዶር፣ የሱፍ ልብስ ስራ፣ ቺት (ቺግ ባፊ)፣ ጃጂም፣ ኤህራሚ ባፊ እና ጊቬህ ዱዚ በሴቶችም ሆነ በወንዶች የሚሰሩ የኢላም የእድ-ጥበብ ውጤቶች  ናቸው።[2]

ኮራሳኔ ጀኑቢ[edit]

ኮራሳኔ ጀኒቢ (የኮራሳን ደቡብ) በኢራን በስተምስራቅ ሲገኝ ከአፍጋኒስታን ጋር በስተምስራቅ ይዋሰናል። በዚህ አካባቢ ያሉ ከፍተኛ ቦታዎች ከሰሜን ምዕራብ እስከ ደቡብ ምስራቅ ባሉ ቦታዎችና በአፍጋኒታን ድንበር እንዲሁም ከኦሲስታን ሜዳማ አካባቢዎች በስተሰሜን ይገኛሉ። እነዚህ ከፍተኛ ቦታዎች በሰሜን ያሉትና 2,857 ሜ የሚረዝሙት የቃኤናት እና የሳርያን ተራሮች፤ በመካከል የሚገኙትና 2,787 ሜርዝመት ያላቸው ፣ ሞሜን አባድ እና ሻህ ተራሮ፤ በስተደቡብ  የሚገኙትና 2,633 ሜ እርዝመት ያላቸው የባራን፣ ኤስቴንድና ሶርክ ተራሮች ተብለው በሦስት ይከፈላሉ። በተራሮቹ ስንሰለት ውስጥ አለፍ አለፍ ብሎ ሜዳማ ስፍራዎች አሉ። ለምሳሌ የቢርጃንድ ቦታ በባቄላንና በሞሜን አባድ ተራሮች መካከል የሚገኝ ትልቅ ሜዳ ነው። ደረቀማ አየር፣ ዝቅተኛ የዝናብ መጠንና ከፍተኛ የሆነ ትነት መኖራቸው የውሃ እጥረት በዚህ አካባቢ እንዲኖር አስችለዋል። የሹር ቃኤንና ሀጂ አባድ ወንዞች፣ የዳሬህ፣ ኦመርሻህና ኦላንግ ኮሆዎች እንዲሁም የጊዮክናቻርዳህ ፏፏቴዎች ከአንዳንድ ጉድጓዶች፣ ቃናት እና ምንጮች ጋር ተደማምረው ብቸኞቹ የኮራሳኔ ጁኒቢ የውሃ መገኛዎች ናቸው።


እንደ ዳቅ ያሉ በፊት ሀይቅ የነበሩ ኋላ ላይ ግን የደረቁ፣ በረሃ እና ከታሪክ በፊት የነበሩ እንሰሳዎች የእግር ዱካ መገኛ መሆኑ ይህን አካባቢ በጣም ልዩ ያደርገዋል። በፓህላቪ ቋንቋ እክስዋራሳን (ከራሳን) ማለት የፀሀይ መውጫ (ምስራቅ) ማለት ነው። ኮራሳኔ ጆኑቢ ሳካርት የሚባለው የኢራን ጥንታዊ ጎሳ መገኛ ነች። በመልከአምድራዊ ገፅታዋና በአየር ፀባይ ምክንያት ኮራሳኔ ጆኑቢ ብዙ የውጭ ጎብኚዎችን መሳብ አልቻለችም። በመሆኑም የዚህ አካባቢ ሰዎችና ቋንቋቸው ለዘመናት ሳይነካ ይገኛል። ብዛት ያላቸው መስኮችና ተራሮች ለኮርሳኔ ጀኑቢ ጥሩ የመኖሪያ ሁኔታን አመቻችቶላታል። አርብቶ አደሮቹ 12% ሲሆኑ በተለያዩ ሥፍራዎች ተሰራጭተው ይገኛሉ።

የዚህ አካባቢ ባህልና እምነት ከተቀረው የኢራን አካባቢ ጋር ከሞላ ጎደል ተመሳሳይ ነው። በቃኤን ህዝቦች የተለመደው ሥነ-ስርዓት ካቦል የሚባል ሲሆን በክረምት የመጀመሪያ ምሽት ላይ ይከበራል። ይህ በአል ለማመስገን ታስቦ የሚደረግ ሲሆን በጭብጨባም ይታጀባል።

ኮራሳን የሚባለው ሙዚቃ የኢራን የጥንት የዘፈን ስልት ሲሆን በሞቀ ዳንስም ይታጀባል። ትንሿ የቢንጃን ከተማ ከድሮ ጀምሮ በተለያዩ ጭፈሪዎች እና ዘፈኖች ትታወቃለች። በተለይ ደግሞ ባለ 5 ቢት (ምት) ያለው ዘፈን የተለመደ ነው። ይህ ሙዚቃ በሌላ አካባቢ አይታወቅም። በተጨማሪም በእንጨት በመታገዝ የሚጨፈር ዘፈንም አለ። የሙዚቃ መሣሪያዎቹን ዘፋኞቹ እራሳቸው የሚያዘጋጁት ሲሆን እነዚህም ዶሆል፣ ሶርና፣ ታምቡር እና ፓይፕ ናቸው።

ኮራሳኔ ጀኑቢ እንደ ባሪቤሪና ሳፍሮን ያሉ ወድ ምግቦችን ስላሏት የቀዩ የወርቅ ምድር ትባላለች። የሚከተሉት ምግቦች የዚህ አካባቢ ተወዳጅ ምግቦች ናቸው፡- ፓሜግራንቴ፣ ቦካራ ፕለም፤ጁጁቤ፣ የሎው ካሽክ፣ ኩሚን ካሽክ፣ የደረቀ ኮክ፣ ቃራህኝ ቆሩት፣ ሌንቲል ኤሽኬንህ፣ ፕለም ኤሽኬንህ፣ የቲማቲም ኤሽኬህ፣ ቃቶቅ አዳስ፣ ሩቫር ካርዴህ ናን፣ ቻርኪ ናን፣ ኮሉቼህ ቃንዲ፣ ካሌህ ካኑ፣ ኖውጁሽ፣ ታፍታን፣ ሮጋንጁሽ፣ ኮማጅ፣ ዛርዲ፣ ጋቫርስ፣ ማሸላ፣ ሳማኑ እና ሻልጋሚ።


ቢርጃንድ አጠገብ በምትገኘው የሙድ መንደር የምንጣፍ ሥራ ይከናወንባታል። የሙድ ምንጣፍ ኢራን ውስጥ ካሉ ምንጣፎች ሁሉ ውዱ ነው። የሱፍ ምርቱ፣ ጥሩ የሆነ የማጠብያ ሂደት፣ ቆንጁ የሆነ የፈተለና የአሰራር ሁኔታው የዚህን አካባቢ ምንጣፎች በአለም ዳርጃ ትልቅ ስም አሰጥቶአቸዋል።

ዶሮክሽ ሌላኛው ታዋቂ የምንጣፍ ማምረቻ አካባቢ ነው። እዚህ የሚሰሩ ብዙ ምንጣፎች በኢራን ምንጣፍ ሙዚዮምና በአስታኔ ቆድሴ ራዛቪ ስበሰብ ውስጥ ይቀመጣሉ። ፓርኬሀ ባፊ የሚባለው ሽመና የዚህ አካባቢ ታዋቂ ባህል ነው። ቃዲፌህ፣ ቦቅባንድ፣ ቻዶር ሻብ፣ ሳራቅ፣ ሳፊ፣ ደስታረካን፣ ቻሃር ፓሻሌህ፣ ካርባስ እና ሎውንግ ተጠቃሾቹ የጨርቃጨርቅ ምርቶች ናቸው። እንደ ሻልጋም ሹይ፣ ካርቤህ ታዝ፣ የወፍ ማኖሪያ፣ ካባሬህና ካልክቢዝ ያሉትን ሰጠራዎች ለመስሪያነት የ‹‹ዊሎ›› ዛፍ ለስላሳ ቅርንጫፍን ይጠቀማሉ። የሸክላ ስራ፣ ፈተላ፣ የነሀስ ሥራ፣ አንጥረኛ፣ የሱፍ ስራ፣ ዚሉ ባፊ፣ ኖውጋን ዳሪ፣ ጃጂም ባፊ፣ ዳባጊ፣ ምንጣፍ፣ ጥልፉ፣ ማሊሌህ ዲዚ እና ቆላብ ባፊ የኮረሳኔ ጆኑቢ ነዋሪዎች ሞያዎች ናቸው።[1]

ኮራሳኔ ራዛቪ[edit]

ኮራሳኔ ራዛቪ የምትገኘው በኢራን ሰሜን ምስራቅ አካባቢ ነው። ከቱርክሜኒታንና አፍጋኒስታን ጋርም በስተምስራቅ በኩል ትዋሰናለች። በረሃማና ከፊል በረሃማ የአየር ፀባይ አሏት። ከ 3000 ሜ በላይ የሚደርሰው የላቲቲዮዱና አልቲቲዮዱ ልዩነት ‹‹120 ቀናት›› አቧራ ያዘለ ነፋስ እንዲኖር አድርጓል። ይህም የአካባቢው የአየር ፀባይና በረሃማነት እንዲጨምር አስችሎታል። በስተሰሜን በኩል የኮፔህ ዳግ ተራራ (3040 ሜ ከፍታ ያለው) እና የኣላ ዳግ ተራራ (ቢናሉድ) ይገኛሉ። ሜዳማ ሥፍራዎች በኣፈር መሸርሸር የተፈጠሩ ናቸው። በከራሳኔ ራዛቪ ትልቁ ሜዳማ ስፍራ የሚባለው 140 ኪሜ ርዝመትና 20 ኪሜ ስፋት ያለው የማሻድ ሜዳ ሲሆን በሄዛር ማሳጂድ እና በቢናሉድ ተራሮች የተከበበ ነው። የእፅዋት አይነቶችን ስናይ ደኖች፣ የግጦሽና ቁጥቋጦዎች ናቸው።  ለመድሃኒትነት፣ ለምግብ እና ለፋብሪካ ከሚጠቅሙ ተክሎች ይልቅ ለግጦሽ የሚጠቅም ተክል በብዛት ይገኛል። 60 በመቶ የሚሆነው የበርሃማና ከፊል በርሃማ ስፍራ ለግመል እርባታ ጠቃሚ ነው። በኮራሳኔ ራዛቪ እንደ ኤምብሪዮ ተራራ፣ የውሃ መፍለቅያዎች እና ያርዳንጎች መኖራቸው የሚያምር የመሬት ገፅታ ቸሮታል። በርሃማና ደረቅ የሆነ የአየር ፀባይ ስለሆነ የውሃ እጥረት አለ። በመሆኑም የውሃ መገኛዎቹ የሚከተሉት ናቸው። አትራክ፣ ካሽፉ፣ሩድ፣ ዶሮንጋር፣ ራንግላንሉ፣ ጃም፣ ካሌሹ እና ሼሾ ታራዝ ወንዞች፤ እንዲሁም ምንጮችና ኩሪዎች።

አርኪኦሎጂስቶች የኮራሳኔ ራዛቪ ታሪክ እስከ 800,000 አመት እንደሚደርስ ይናገራሉ። ከክርስቶስ ልደት በፊት በ600 በአካሜኒድ ሀይሎች ተጠቅታ ነበር። ኋላ ላይ ደግሞ ለሳሳኒድና ፓርቲን ኢምፓየሮች ተገዝቷል። በፓርቲያን እና ሰሳሚድ ሰርው-መንግስታት ኮራሳን ትልቁ ፐርሺያን ከመሰረቱት አራቱ አካላት መካከል ነበረች። እስልምና ሲገባ ደግሞ የኢራን መንፈሳዊና የስነ-ፅሁፍ ማማ መሆን ቻለች። ኢማሞ ሬዛ ማሙንን ተተኪነት ለመቀበል ያደረገው ግብዣና ሆላ ላይም በ818 በከራሳኔ መስዋቱ ኮራሳኔ ራዛቪን ታላቅ የታሪክ ሀገር አንድትሆን አደረጋት። የተቀደሰው የኢማም ሬዛ በማሸሃድ ከተማ መገኘቱ አካባቢውን በኢራን ብቻ ሳይሆን በአለም ላይ የሚገኝ ትልቁ የዝየራ ቦታ አድጓታል።

በኮራሳኔ ራዛፊ ግዛት የተለያዩ የኑሮ ዘይቤ ያላቸው ብዙ ጎሳዎች መገኘታቸው ትልቅ ዋጋ አለው። በኢራን ሰሜን ምስራቅ አካባቢ ቱሪክሜን ጎሳዎች ዋና ህዝቦች ናቸው። በአካባቢው በስተሰሜንና በስተደቡብ አቅጣጫ ሰፍረው የሚገኙም ካሉቺ፣ ኩርዶች፣ ሉሮች እና አረቦችም አሉ።

የተወሰነ ልዩነት ቢታይበትም የዚህ ግዛት ብሄራዊና ሃይማኖታዊ በዕላት ከሌላው አካባቢ ጋር ተመሳሳዮች ናቸው። ቻሃርሻንቤህ ሱሪ የሚባለው ክንውን አመድ በንፋስ እንዲወስድ ይደረግና ጀበና፣ ከሰል፣ ጨውና ሳንቲም ከጣራ ላይ በመጣል መጥፎ መንፈስን ያባርራሉ። ከጫወታ አይነቶች ደግሞ አርሃንግ፣ ሀጎርጎሪ፣ ኦስታድ ሴህፓ እና ጃምቡር አቪዜህ በእረፍት ጊዜ ይዘወተራሉ።

ኮራሳኔ ራዛቪ በጣም ውብና ሰፊ  ሙዚቃ ካለቸው አካባቢዎች አንደኛዋ ናት። በቶርባቴ ጃም አካባቢ ያለው ሙዚቃ ግን ምንጊዜም የተለየ እንዲሆን ይታሰባል። ታር፣ ሶርና፣ ቁሽሜህ፣ ዳሆል እና ‹‹ፒፔ›› የሙዚቃ መሳሪያዎቻቸው ሲሆኑ በውድን ሆርስ (ጎናባድ)፣ አፓር (ቶርባቴ ጃም) እና ‹‹ዳጋር›› (በቱርኮሜን ጎሳዎች) ዳንሶች ይታጀባል። በዚህ አካባቢ የሚዘወተረው ምግብ የመረቅ አይነት የሆነው አሽ ነው። ይህ ምግብ የተለያየ መልክ አለው። እነዚህም ለበሽተኛ ፈዋሽ የሆነው አቡ ዳርዳ፣ የተለያዩ ቅርፅ ባላቸው ቂጣዎች የሚባሉት ጉሽቫሬህና ላክሻክ፤ ባልኑሬ ቶርሽ እና በማር፣ ዱቄትና እንቁላል የሚቀርበው ጁሽ ፓሬህ ናቸው። ከነዚህ ምግቦች በተጨማሪም ኤሽኬነህ፣ ቱጊ፣ ዲዚሳንጊ፣ እና ጎርማስ                                          ታዋቂ ምግቦች ናቸው። ኮርሳኔ ራዛቪ ተወዳጅ ጣፋጭ ምግቦችም አሏት። እነዚህም ደቫዝዳህ፣ ኤማምሃልቫ፣ ሩቫር ካንዴህ፣ ቄሌፍቲ፣ ቆታብ፣ ኮልጅና ማቁት ናቸው። መስገጃ፣ መስገጃ ድንጋይ፣ ሙስብሃ፣ ሽቶ፣ ቅመሞች፣ ‹‹ባርቤሪ›› እና ‹‹ሳፉሮን›› በዚህ አካባቢ በስፋት የሚገኙ ስራዎች ናቸው።

የግመል ጨርቅ ስራ ( ባራክ ባፊ)፣ ምንጣፍና ኪሊም፣ የሀር ሽመና፣ ቱር ቆይሴ (ባኔይሻቡር)፣ የሸክላ ሥራ ፣ የእንጨት ጠረባ ፣ የቆዳ ውጠራ (በሻንዲዝና በቁቻን)፣ የጌጣጌጥ ስራ፣ የማሽቆጥቆጥ ሥራ፣ የጡብ ማምረት፣ ሼር ባፊ፣ የቅርጫት ሥራ፣ የቅብ ሥራ፣ የነሀስ ሥራ እና አርካቫን ባፊ የኮርሳኔ ራዛቪ የዕደ-ጥበብ ውጤቶች ናቸው።[1]

ኬርማን[edit]

የኬርማን ግዛት አጅግ ከፍተኛ የሆነ በርሃማነት ያለው ሲሆን በኢራን በስተደቡብ ምስራቅ ይገኛል። ከኢራንም 11 በመቶ የሚሆነውን ስፍራ ይዟል። ዝቅተኛ አርጥበትና የዝናብ መጠን፣ በጣም ከፍተኛ የሆነ ትነት እና በቀኑና በማታው ጊዜ ያለው የአየር ሁኔታ በጣም የተለያየ መሆን የኬርማንን የአየር ፀባይ ከፍተኛ በርሃማ እንዲሆን አስችሎታል። ይህ በርሃማነትም በኬርማን ያሉ የከርሰምድርና በመሬት ላይ የሚገኝ ውሃን ዋነኛው የውሃ መገኛ አድርጎታል። የቻሪ፣ ሳዒዲሴኮንጅ፣ ታህሩድ፣ ዴራክታንጋን፣ ቲግራንና ሃንጃም ቆርሻብ ሄቅ እና የሲማክና ኤሽቅ ኣባድ ፏፏቴቶዎች የኬርማን የውሃ መገናኛዎች ናቸው። ከፍተኛነት ያላቸው የኬርማን ተራሮች የዛግሮስና የኢራን የመካከለኛው ተራሮች ሰንሰለት አካል ናቸው።  በአካባቢው ያለውን የእርጥበት ሁኔታ ላይ የፓልቫር፣ የኩህፓዬህ፣ የጁፓር እና የባዳሙ ተራሮች ተፅዕኖ ያሳድራሉ። የዚህ አካባቢ ውስን የሆኑ ተክሎች የበርሃ ተክሎችና እንደ ‹‹ስኮፓሪያ››፣ ተማሪስክ›› እና ‹‹ ሚልክቬታች›› ያሉ ዛፎች ናቸው። እና ቦሬጅ›› እና ‹‹ትራጋካንዝ›› በኬርማን አልፎአልፎ የሚገኙ ለኢንዱስትሪና ለመድሃኒት ቅመማ የሚሆኑ ተክሎች ናቸው። ምንም እንኴ አስቸጋሪ የአየር ፀባይ፣ በረሃና የመሬት መሸርሸር ቢኖርም የአካባቢና የመሬት ጎብኚዎችን ( eco-tourism/geotourism)  ግን መሳብ ችሏል።

ከእስልምና መግባት በፊት ኬርማን ‹‹ኬርማና›› እና ‹‹ኬርማኒያ›› ትባል ነበር። በዚህ አካባቢ የነበረው የመጀመሪያው ሰፈራ የተከናወነው ከእየሱስ ልደት በፊት በ4ኛ ሺህ ጊዜ ነበር። ኬርማን በተለያዩ ጊዜያት አስደሳችንና መጥፎ ነገርን እንዲሁም ብዙ ውጣ ውረድን አስተናግዳለች። ሆኖም ግን እጅግ ጠንካራ ሰራተኛና ትጉህ የሆነው ህዝቧ ችግሮችን ሁሉ በውጤታማነት ሊወጣቸው ችሏል።

ኬርማን በኢራን ውስጥ ካሉ ግዛቶች ለአርብቶ አደሮች መኖሪያነት በመጥቀም ሁለተኛው ነው። በዚህ አካበቢ ያሉ ጎሳዎች የፐርሺያ፣ ቱኪሽና ባሉቺ ቋንቋዎችን ተናጋሪዎች ናቸው። ሁሉም የየራሳቸው የሆኑ ዘፈኖችና ጭፈራዎች አሏቸው። ይህ አይነቱ የጥበብ ስብጥር በይበልጥ በጂሮፋት፣ ካህኑጅ፣ ባም፣ ሲርጃን፣ ዛራንድ፣ ባፉት፣ ሻህሬ ባባክ እና ባርዲሲር በግልፅ ይታያል። እንደ ቃላንዳሪ፣ ካንቃሂ፣ ሀይማኖታዊ፣ ሳሬባኒ፣ ‹‹ሊሪክስ››፣ ቃሊባፉ ካኔህ፣ ሩዝናሜህ እና የህፃናት ዘፈኖችን በዚህ አካባቢ ለመጫወቻነት የሚያገለግሉት ባህላዊ መሣሪያዎች ዶሆል፣ ጁሬህ፣ ዳኘ፣ ዳራክ፣ ዳማም፣ ናቃሬህ፣ ኔይ ማሽኪ፣ ቻንግ፣ ራባብ፣ ቦንጁ፣ ቶንበክ ወዘተ ናቸው። ከዘፈን በተጨማሪም የዚህ አካባቢ ጭፈራም ቢሆን ለምሳሌ ቹሃብ በሀገር ደረጃ የሚታወቅ ነው።


በኬርማን እንደ ሳዴህ ያሉ በሀገር ደረጃ የሚከበሩ ክበረበዓላት አሉ። ይህ ክብረ በዓል የሚከበረው በጃኑዋሪ 30 ሲሆን የዞራስታሪያን እምነት ተከታዮች ሁሻንግ የሚባለው የአፈታሪኩ ንጉስ እሳቱን ያገኘበት ጊዜ ነው ብለው ያምናሉ።


ሰው ተቀባይ የሆኑት የኬርማን ነዋሪዎች ለሚጎበኟቸው እንግዶች የሚያቀርቧቸው ምግቦች እነ ሞታንጄህ አብጎሽት፣ ካሌህ ጁሽ እሽ፣ ቦዝ ቆርሜህ፣ ሃሊም ባዴም ጃን፣ ቻግማል፣ ኦማች እና ቃቶቅን ናቸው። ብዙም እጅ የሚያስቆረጥሙ ፓስቲዎች አሉ። እነዚህም ኮሎምፔህ፣ ሀጅ ባዳም፣ ቤሬቨቱ፣ ሀልዋ፣ ፋሉዴህ ኬርማን፣ ዛቡን ሚርዛ፣ ጎቫቱ እና ናን ፓር ናቸው።

በጥንታዊው የሻህዳድ አካባቢ በተደረገ የአርኪኦሎጂ ቁፈራ የተገኙት ውድ ቁሶች እንዳመላከቱት የኬርማን አካባቢ ነዋሪዎች ዕደ-ጥበቦቻቸውን ወደ ተለያዩ የአለም ክፍል ይልኩ ነበር። የ5000 አመታት እድሜ ያለው የኢራን ባንዲራ በመገኘቱ በኢራን ሙዚዬም ውስጥ ተቀምጧል። የራዮን ምርቶች ወደ ግብፅና ህንድ ይላኩ ነበር። ከድሮ ጀምሮ የኬርማን ምንጣፎች የብዙ ቤተ-መንግስትን ግድግዳና ወለሎችን ሲያሳምሩ ኖረዋል። እንዲሁም የኪሊምና ፓቴህ ሥራዎች የዚህ አካባቢ ጥበብ ታዋቂ ምርቶች ናቸው። የቢላዋና የጠመንጃ ሥራ (በላዬን አካባቢ)፣ የወረቀት፣ የሸክላ፣ የነሀስ ማቅለጥ፣ የሽመና እና የመሳሰሉ ሥራዎች የኬርማን ህዝብ የጥበብ ውጤቶች ናቸው። [1]


ኬርማንሻህ[edit]

ኬርማንሻህ  በኢራን በስተምዕራብ ስትገኝ ከኢራቅ ጋር ከ330 ኪ.ሜ በላይ ርዝመት ያለው ድንበር ትወሰናለች። ወጥ ያልሆነው የመሬት አቀማመጥና የሜድትራንያን ንፋስ የወይናደጋ አይነት የአየር ፀባይ እንዲኖር አስችለዋል። በመሆኑም የምዕራብ ንፋስ (ዛላን)፣ የሰሜኑ ንፋስ እና ሳም (ሳሙም) ንፋስ የኬርማንሻህ የአየር ሁኔታ ላይ ተፅዕኖ ፈጥረዋል። የዚህ ግዛት ከፊል ተራራማ ስፍራ በአብዛኛው በዛግሮስ የተራሮች ሰንሰለት የተሸፈነ ነው። በተወሰነ ስፍራዎችም ቢሆን ሜዳማና በደለል የተሞላ ቦታ ይገኛሉ። ዳላሁ፣ ሻሁ፣ሰፌድ ኩህ፣ አታሽጋህ (አታሽካዴህ)፣ ፓራቭ እና ባሞ ትላልቆቹ ከፍተኛ ስፋሮች ሲሆኑ ሳህኔህ፣ ሃርሲን፣ ቢልቫር፣ ዲንቫር፣ ማሂዳሸት እና ኬሬንድ ደግሞ ደለላማ ቦታዎች ናቸው። የመሬቱ አቀማመጥና የአየር ፀባዩ መለያየት የተለያዩ የአፈርና የአትክልት አይነቶች እንዲኖሩ አስችሏል። በመሆኑም የዱሩ ኦክ ዛፉ ከአርማናት እስከ ዛርየቤላን እና ሃሊላን አካባቢዎች ድረስ በብዛት የሚገኝ የተክል አይነት ነው። ሌሎቹ ተክሎች ደግሞ የዱር ፒስታኪዩ፣ የዱር አልሞንድ፣ ፈግ እና የራፕቤሪ ዛፍ ናቸው። ከአትላንቲክ ወደ ሜዲትራንያን ውቅያኖስ የሚነፍሰው ነፋስ፣ ከፍተኛ የሆኑ ተራሮች መኖራቸው እና በቂ የሚባሉ የዝናብና የበረዶ መጠን መኖራቸው በቂ የሆነ የውሃ ሀብት እንዲኖርና እንደ ቃራህሱ፣ ጋማሲያብ፣ ዲነቫር፣ ሜርግ፣ ራዛቫር፣ ጃሚሻን፣ ሲርቫን እና አልቫንድ ያሉ ወንዞች እንዲፈጠሩ ምክንያት ሆነዋል። ብዛት ያለው የውሃ መጠን ያላቸው የውሃ ምንጮች ስላሉም ለቱሪስት መስእቦች የሚሆኑ የመዝናኛ ስፍራዎችን ማቋቋም ያስችላሉ። ከነዚህ ምንጮች መካከል ቃንባር፣ ኬዝር፣ ዛንድ፣ ሪጃብ፣ ያቫሪ፣ ቢሶቱን፣ ሙርት እና ኒሉፋር ትላልቆቹ ናቸው።


የኬርማንሻህ ነዋሪዎች በቅድመ ታሪክ ዘመን ከነበሩ ቀደምቶች ስፋሪዎች አንደኞቹ ናቸው። ከድሮ ጀምሮ ብዙ ህዝብ ከሰፈረባቸው በዛግሮች ከሚገኙ ቦታዎች አንዱ ነው። ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ለአሳሪን ከአሳሪያን ግዛት አጓረባች በመሆኗ ለተለያዩ ጥቃቶች የተጋለጠች ነበር። በአካሜኒድ ስርወ-መንግስት ጊዜ ኬርማንሻህ ከኤክባታና እስከ ባቢሎን የተዘረጋው የንጉሳዊ ጎዳና አካል ነበረች። በፐርሺያን ኢምፓየር ጊዜም ጥንታዊቷ የቢሶቱን ከተማ ከትላልቆቹ አስተዳደሮች አንደኛዋ ነበረች። የኬርማንሻህ ወርቃማ ጊዜ የሚባለው ንጉሶቹ በክረምት ወቅት እንደ መዝናኛነት ይጠቀሙባት በነበረችበት በሳሳኒ አምፓየር ጊዜ ነበር። የኬርማንሻህ ከተማ እንድትቆረቆር ምክንያት የሆኑት እንደ ሆልቫን ያሉ ከተሞች መመስረታቸውና በምዕራባዊው የፐርሺያ አካባቢ የሳሳኒድ መንግስት ይከተሏቸው የነበሯቸው የከተማ ፓሊሲዎች ናቸው ። ከዚህ ጊዜም ጀምሮ የኬርማንሻህ ነዋሪዎችን ይህ አይነቱ የተመቻቸ ሁኔታ አግዟቸዋል። እንዳንድ ሰዎች ኬርማንሻህ ስያሚዋን ያገኘችው ከተማዋ አንድትገነባ ያዘዘውና የኬርማን ከተማ ገዢ በመባል ከሚታወቀው ከ388 እስከ 399 ድረስ ከነገሰው የሳሳኒድ ንጉስ ባህራም አራተኛ ስም ነው። እንደ ኮርዴስታን ህዝቦችም የኬርማንሻህ ህዝብ የአርያን ዘሮች ሲሆኑ በኢራን ከፍተኛ ቦታዎች የሰፈሩ የጥንት ህዝቦች ናቸው። ወደ ኢራን ገብተው በዛግሮስ ተራራ ሰንሰለት ላይ መስፈር  የጀመሩት ከክርስቶ ልደት በፊት በ2ኛው ሚሌኒየም ነበር። አብዛኞቹ ኬርማሻንህ ነዋሪዎች በሰሜን ምዕራብ የኢራን አካባቢ በሰፊው የሚነገረውን የኩርዲሽ ቋንቋ ይናገራሉ። ከብዛኛዎቹ መካከል ደግሞ ካልቦሪ፣ አራሚ፣ ሱራኒ እና ለኪ የሚባሉት በኬርማንሻህ ነዋሪ በሆኑት ኩርዶች ዘንድ ይገኛሉ።

እንደተቀሩት የኢራን አካባቢዎች ሁሉ አዲሱ የኩርዲ አመት (ኖውሩዝ) የሚከበረው በፀደይ የመጀመሪያ ቀን ነው። ሆኖም ግን የራሳቸው የሆነ የጊዜ አቆጣጠር ያላቸው ሲሆን የሚከበረውም በፊብሩአሪ 20 ነው። የካልቦ ጎሳዎችም የራሳቸው የጊዜ አቆጣጠር ዘዴ ሲኖራቸው በ45ኛው የክረምት ወቅት ማለትም በፌብሩአሪ 4 የአዲሱ አመታቸው ነው። ቫሃር ኩርዲ በመባልም ይጠሩታል። ካሌንደሩ 360 ቀናት ያሉት ሲሆን የተቀሩት 5 ቀናት ማለትም ከኤፕሪል 3 እስከ ኤፕሪል 7 ድረስ ያሉት ቀናት ደግሞ ፓንጄህ ይባላሉ። የኬርማንሻሂ ነዋሪዎች ብሄራዊና ባህላዊ የሆኑትን የአዲስ አመት በዓላት የሚያከብሩት በልዩ ሁኔታ ነው። ኩላክ ቤንማ (ኦታሽ አፍሩዝ) የሚባሉት በአዲሱ አመት ጊዜ በቡድን ሆነው በጎዳና ላይ በመዘዋወር የፀደይ ጊዜ መቃረቡን በጭፈራ የሚያበስሩ ሰዎች ናቸው። ወጣቶች ደግሞ ልብስ የሚወራወሩበትን (ሻል ዳራኪ) ትዕይንት ይተገብራሉ። በአዲሱ አመት ዋዜማ ወጣቶቹ በጎረቤታቸው ቤት ጣራ ላይ በመወጣት ረጅም ልብስ በመስቀል የአዲስ አመት ስጦታን ይጠባበቃሉ። ቀደም ባሉት ጊዜያት ግን ስጦታ ይሰጣቸው የነበሩት በበዓሉ ዋዜማ ድንኳን ተጥሎ ነበር። በዚህ ጊዜያት ሀብታምና ታዋቂ የሆኑ ሰዎች በበራቸው ላይ ሁለት የዱር ፍየል ቀንዶችን በመስቀል  ህብረተሰቡ ውስጥ ያላቸው ክብር ያሳዮ ነበር። የሀብታም ቤት መሆኑን ያወቁ ወጣቶችም ስጦታቸው እስከሚሰጣቸው ድረስ ድንኳናቸውን አይነቅሉም ነበር።

የኬርማንሻህ ዘፈኖች ጀግንነትንና ጀበዶኛነትን የሚያንፀባርቁ ናቸው። ሁራህ የሚባለው ዘፈን በታምቡር የሚዘፈን የቆየ ዘፈን ነው። እንደሚነገረው ከሆነ የሁራህ ዘፈን ባርባድ የሚባለው ጎበዝ የፍርድ ቤት ዘፋኝ ለኩስ ሮው ሁለተኛ ለንግስት ሺሪን ይጫወትላቸው ነበር። ሙዮህ (ሙር) የሚባለው ዘፈን በሀዘን ጊዜ የሚባል ነው። በኋላ ላይ ሁራህ ሱዝ የሚባል የዘፈን ዜማ ተሰጠው። ብዙ ጊዜ ግን ሁራህ የሚዘፈነው በኩርዶች በወጊያ ጊዜ ነው። ሌላኛው ሙዚቃ ጎራኒ የሚባል ሲሆን በሼምዳል በመታጀብም ሳይታጀብም በሰርግ ወቅት ይዘፈናል።  ሲያህቻሜኔህ የሚባለው ሙዚቃም ሌላኛው ተወዳጅ ዘፈን ነው። የኩርዶች የጭፈራ ስልት በኬማንሻህም ይገኛል። ደዝላህ፣ ታምቡር፣ ሶርና፣ ሼምሻል፣ ቶንባክ እና ደሆል በሚባሉ ባህላዊ ዘፈኖች ይታጀባል።  በኬርማንሻህ ያሉ ተወዳጅ ምግቦች ኮማር እሺ፤ ደቪኔህ፣ ኮሬሼ ካላል ባዳም፣ ፓራሽት፣ ጃርጎ ቦዝ፣ዞርዴህ፣ ሲብ ካሬህ፣ ዙቫ ካሬህ እና ሻልሚን ናቸው። እንደ ስጦታነት ከኬርማንሻህ የሚወሰድ የምግብ አይነት ደግሞ የኬርማንሻህ የቅቤ ክሬም ነው። የኬርማንሻህ ጣፋጮች ቻንጋል፣ ናኔ ቤሬንጂ፣ ናኔ ሼካሪ፣ ካክ፣ ናኔ ኮርማዮ እና ናኔ ሮጋኒ ናቸው።

የኬርማንሻህ የእደ-ጥበብ ውጤቶች የሚባሉት የሚከተሉት ናቸው፡- ጊቬህ ኬሺ፣ ሞጅ ባፊ፣ የመጋረጃ ሥራ፣ ቺግ ባፊ፣ ቀረፃ፣ የብረት ሥራ፣ ኪሊም ባፊ፣ የሱፍ ሥራ፣ ጃጂም እና የምንጣፍ ሥራ[1]

ኩዜስታን[edit]

ኩዜስታን በኢራን ደቡብ ምዕራብ ስትገኝ በምዕራብ ቡኩል ከኢራቅና ኪዌት ጋር ትዋሰናለች። ሁለት አምስተኛው የሚሆነው ክፍሏ ተራሪማ ነው። የዛግሮስ ተራራ ሰንሰለት ደቡባዊ ክፍል ደግሞ ሁሉንም የዚህን ግዛት ሰሜናዊውንና ምስራቃዊውን ክፍል ይሸፍናል። 36,000 ሜ ርዝመት ያለው የመንጋሽት ተራራ ትልቁ ነው። የዚህን ግዛት 3/5ውን የሚሸፍነው የኪዜስታን ደለላማ ዳርቻዎች ከዛግሮስ ተራራ ወደ ፐርሺያ ባህረ ሰላጤና አርቫንድ ረገድ ባህር የተዘረጋ ነው። የሚከተሉት ጉዳዮች የኪዜስታንን የአየር ፀባይ የሚወሰኑ ናቸው። በኡኮቴር አካባቢ የሚገኘው የአየር ግፊት፣ ከፍተኛ አየር፣ የዛግሮች ተራሮች፣ ለአረብ በረሃዎችና ለፐርሺያ ባህረ ሰላጤ ቅርብ መሆን። ኩዜስታን በጣም ሞቃታማና ደረቅ የአየር ፀባይ አላት። ሆኖም ግን ከሰሜንና ምስራቅ አካባቢዎች ወደ መካከለኛው ደለላማ አካባቢዎች ስንሄድ አየረና የእርጥበቱ መጠን ይጨምራል፤ በፐርሺያ ባህረ ሰላጤ ዳርቻ ደግሞ በጣም ይጨምራል። እነዚህ የአየር ፀባያት፣ የከፍታዎች ልዩነት፣ የአፈሩ አይነትና የመሬቱ አቀማመጥ በኩዜስታን ሰፊ የደን ሽፋንና የተለያዩ የተክል አይነቶች እንዲኖሩ አስችሎታል። 320,000 ሄክታር የሚሆነው የኢራን የደን መሬት የሚገኘው እዚህ ነው። 70 በመቶ የሚሆነው መሬት በአክ ዛፍ የተሸፈነ ነው። እነዚህ ደኖች አየረን በማቀዝቀዝና ለኑሮ አመቺ የሆነ ሁኔታን ለመፍጠር አስችለዋል። በቋሚነትና በጊዜአዊነት የሚበቅሉት ተክሎች በተራራውና በዝቅተኛው ሥፍራ ለሚኖሩ ከብቶች በግጦሸነት ያገለግላሉ። የካርኬህ፣ ዴዝ፣ ካረን (መርከቦች የሚጓዙበት የኢራን ብቸኛው ወንዝ)፣ ጃራሂና ዘህሬህ ወንዛች የኩዜስታንን የውሃ መገኛዎች ናቸው። እነዚህ ወንዞች በአብዛኛው ሊፈጠሩ የቻሉት በዝናብና ከዛግሮስ በሚቀልጡ በረዶዎች አማካኝነት ነው። የከርሰ ምድር ውሃም በሰፊው ስለሚገኝ ኩዜስታንን "የአረንጓዴው ወርቅ ምድር" አስብሏታል። በአጠቃላይ ኩዜስታን የሚያምር የፐርሺያ ባህረ ሰላጤ ዳርቻን፣ ረገረግ ቦታዎችን፣ ዝቅተኛና ሞቃታማ ደለላማ ቦታዎችን፣ ብዙ ሃይቆችን… የመሳሰሉትን ሥለያዘች የተፈጥሮ ተቃርኖን የምታጣጥምና ውበት አድርጓታል።

የኩዜስታን ሥም አመጣጥ ከኩዚ ምድር ጋር የተያየዘ ነው። ኩዚዎች የዚህ አካባቢ የመጀመሪያዎቹ ነዋሪዎች ሲሆኑ ቋንቋቸውም እስከ ላሳጊድ ጊዜ ድረስ ቆይቶ ነበር።ከክርስቶስ ልደት በፊት በ2400 በሱሳ የለላሢቴ ሥልጣኔ ተነሳ። ከክርስቶስ ልደት በፊት በሦስተኛው ሺህ አመት ላይ አብዛኛውን የኢራንን ከፍተኛ ቦታዎች ከናማክ እና ሀለቱ በረሃዎች እስከ ሜሶፓታማያ እንዲሁም ከካስፒያን ባህር እስከ ፐርሺያ ባህረ ሰላጤ ድረስ ተቆጣጥረውት ነበር። ከ522 - 486 ድረስ የነገሰው ታላቁ ዳሪዮስ ሱሳ የግዛቱ ማዕከል አድርጎ አፓዳና የሚባለውን ውብ የድንጋይ ቤተ-መንግስቱን አሳነፀ። በዜሬክሲስ የንግስና ጊዜ ሱሳንን ጨምሮ የኢራን ከተሞች በጣም አብበው ነበር። ሆኖም ግን ይህ ገናናነት እስክንድር ባቢሎንንና ሱሳንን ሲየዝ ከስሟል። ከዚህ በኋላ ሴሊዮሲድ ይህን አካባቢ አስተዳድሮታል። የዚህ አካባቢ ነዋሪዎች ታዲያ በዚህ የብልፅግና ጊዜ እንኳ ለኢራን ያላቸው ታማኝነት አልቀነሰም ነበር። በቅርብ ጊዜም በተለይ በስምንት አመቱና ተገደን በገባንበት የኢራንና የኢራቅ የጦርነት ወቅት የኢራንን ዳር ድነብር ለማስከበር ብለው በመስዋት የድል ተምሳሌት ሆነዋል።

በሰሜን ኩዜስታን አካባቢ አርብቶ አደሮች የሆኑት የሰርሰና የአረብ ጎሳዎች አልፎ አልፎ ሰፍረው ይገኛሉ። የራሳቸው ባህሎች ያሏቸው የአረብ ጎሳዎች የራሳቸው እሴቶችን ጠብቀው ይኖራሉ። አረቦች በክረምትና በበጋ ለሚያደርጉት ስደት የሚጠቀሙበትን ድንኳን የሚሰሩበት ጥበብ ሲያህቻዶር ባፊ ይባላል። ጠቅለል ባለ መልኩ ስናኘው በጣም ቀላል የሆነ የአኗኗር ዘይቤ  ያላቸው የአረብ ጎሳዎች ትልቅ፣ ዘመናዊና ውስብስብ የነዳጅ ማጣሪያ እንዱስትሪ ማዕከል ከሆኑት የአባዳንና ሰሌይማን ቦታዎች አጎራባች መገኘታቸው የሚገርም ስብጥርን ይፈራል።

በኩዜስታን የሚኖሩ አረቦች፣ ሱሮችና ሌሎች ጎሳዎች የራሳቸው የሆኑ ክበረ በዓላትና ባህሎች አሏቸው። ለምሳሌ የሹሽታር እና ዴዝፍል አካባቢ ነዋሪዎች ከሌሎች ዒዶች በተጨማሪ የዞል ሂጃን የመጨረሻ አርብን ያከብራሉ። ቀጣዮቹ ሁለት የሙሀረምና ሶፈር ወሮች የሃዘን ጌዜያቸው ናቸው። በድሮ ጊዜ ሰዎች እየዘፈኑና እየጨፈሩ ያመሹ ነበር። በዚች ምሽት የቪኑስ ኘላቴት ጁፐተር ጋር ትደርሳለች ብለው ስለማያምኑ የተሳሉት ሁሉ ይሳካል ይላሉ። በዙልሂጃ ወር በየአመቱ የሀጅ እና ቤይራቅ ዛናን ስነስርአቶች ይከወናሉ። በሄንዲጃን ስንዴ ምርቶቻቸውን አጭደው ከወቁ በኋላ የደስ ደስ በአል ያዘጋጃሉ። በአዲሱ አመቱ የ13ኛው ቀን (ሲዝዳህ ቤዳር) ሁለት ጊዘ ያከብራሉ። አንደኛው የመጀመሪያው የ13ኛው ቀን ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ከዒድ በኋላ ያለው 13ኛው ቀን ነው።

የመጥሙቀ ዮሃንስ ተከታዮች የሆኑ ኩዜስታኖች ራሻሜ የሚባል ልዩ የሆነ የመጠመቀያ ስነስርአት ያክናውናሉ። በዚህ በዓል ላይም ራስቴች የሚባል ልብስ ለብሰው ወደ ካረን ወንዝ ወርደው በየተራ ገላቸውን ይታጠባሉ። ለህፃናት ደግሞ ደክረኒ የሚባል ተመሳሳይ ዝግጅት ይዘጋጃል። ለልጃገረዶችም እንዲሁ የተለየ ኘሮግራም አላቸው። የዚህ እምነት ተከታዮች በተለያዩ ጊዜያት የሚፈፅሟቸው ሌሎች በአላትም አሉ። በኩዜስታን አርበቶ አደሮችና አረቦቹ የየራሳቸው ሙዚቃ አላቸው። በኩዜስታን የሚገኘው የአረበኛ ሙዚቃ በሌላ ሀገራት ካለው የአረበኛ ሙዚቃ የተለየ ነው። ይህ ዘፈን ስለ ጀግንነትና ስለ አይበገሬነት የሚያወሳ ነው። ጉሼ የሹሽታር የሚባለው ሙዚቃ በኢራን ታዋቂ ነው። በዚህ አካባቢ ያሉ ተወዳጅ የሙዚቃ መሣሪያዎች ዳማም፣ ኔይ አንባነ፣ ታር፣ ቶን ባክ፣ ዳዮሮህ፣ ደሆልና ሄዬ ሃፍት ባንድ ናቸው። ኩዜስታኖች ከባህላቸው ጋረ ቁርኝት ያለው የራሳቸው የሆነ የዳንስ አይነትም አላቸው።

ከዜስታኖች ለክረምትና ለበጋ የሚሆኑ የምግብ አየነተች አሏቸው። የአሳ ምግብ በጣም ይዘወተራል። እንዲሁም ቃልዬህማሂ፣ አብጉሸት፣ አብ ጁሻክ፣ ቤንጎ፣ በሽራክ፣ አብ ፒያዚ፣ አብቶርሹ፣ ሱር ባቃላ፣ በሺር ሃላቪ፣ ሃሚስቱሌህ እና ቆልቆል ተወዳጅ የኩዜስታኖች የምግብ አይነቶች ናቸው። ቴምርና የ"ሴሳሜ" ፍሬዎችን በጥምረት ይታወቃሉ። ከእደ ጥበባቸው ደግሞ ዳስትባፊ፣ ጃጂምባፊ፣ ጊቬህ ዱዚ፣ ቹካባፊ፣ የጊኪልን ብር ሥራ፣ የምንጣፍ ሥራ፣ የፐልፍ ሠራ፣ የካባ ሥራ፣ ቻፊዬ

  1. ^ a b c d e Cite error: The named reference :0 was invoked but never defined (see the help page).
  2. ^ Cite error: The named reference :1 was invoked but never defined (see the help page).